ኤሌክትሪክ ተስፋዬ መላኩን በይፋ አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው ኤሌክትሪክ ከሳምንት በፊት ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሶ የነበረው ተከላካዩ ተስፋዬ መላኩን ዛሬ ፌዴሬሽን ወስዶ አስፈርሟል፡፡

ተጫዋቹ ለእረፍት ክፍለ ሃገር የነበረ በመሆኑ እስካሁን ሳይፈርም የቆየ ሲሆን ኤሌክትሪክ ለቀድሞው የወላይታ ድቻ ተከላካይ በ2 አመት ውስጥ 1 ሚልዮን ብር ወጪ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ኤሌክትሪክ በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ከወላይታ ድቻ ተጫዋች ሲያስፈርም ሁለተኛው ነው፡፡ አማካዩ አሸናፊ ሽብሩ ባለፈው ሳምንት ፊርማውን ማኖሩ ይታወሳል፡፡

ያጋሩ