ወደ 2007 የኢትዮጰያ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ የሚደረጉ ጨዋታዎች ዛሬ በባህር ዳር ስታድየም ይጀመራሉ፡፡ ውድድሩን የምታስናግደው ባህርዳር ከተማ 16 ክለቦችን ተቀብላ ያጠናቀቀች ሲሆን ዛሬ በመክፈቻ ስነ-ስርአቱ ለየዞኑ አሸናፊዎች ሽልማት በመስጠት ውድድሩ ይጀመራል፡፡
ከ7ቱ ዞኖች በአሸናፊነት ያጠናቀቁት ሱሉልታ ከነማ (ከማእከላዊ ሀ) ፣ አ.አ. ፓሊስ (ከማእከላዊ ለ) ፣ ባህርዳር ከነማ (ከሰሜን ሀ) ፣ ወልዲያ ከነማ (ከሰሜን ለ) ፣ ሻሸመኔ ከነማ (ከደቡብ ሀ) ፣ ሆሳእና ከነማ (ከደቡብ ለ) እንዲሁም አዳማ ከነማ (ከምስራቅ) ዋንጫ ይቀበላሉ፡፡
የምድብ ድልድሉ ትላንት 9 ሰአት ላይ ይፋ የሆነ ሲሆን በአራት ምድብ የተከፈለው የምድብ ድልድል ይህንን ይመስላል፡፡
ምድብ– 1
.ባህርዳር ከነማ
. አዳማ ከነማ
. ልደታ ኒያላ
. ቡራዩ ከነማ
ምድብ – 2
.ጥቁር አባይ
. ሻሸመኔ ከነማ
. ወልቂጤ ከነማ
. አዲስ አበባ ፖሊስ
ምድብ– 3
.ፋሲል ከነማ
. ሆሳህና ከነማ
. ድሬድዋ ከነማ
. ሱሉልታ ከነማ
ምድብ– 4
.ወልድያ ከነማ
. አዲስ አበባ ከነማ
. ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት
. ደቡብ ፖሊስ
ውድድሩ ዛሬ በአስተናጋጁ ከተማ ክለብ ባህርዳር ከነማ እና አዳማ ከነማ መካከል 9፡00 ላይ በሚደረግ ጨዋታ ይጀምራል፡፡