የብሄራዊ ሊግ የዛሬ ውሎ…

በ2007 ብሔራዊ ሊግ የማጠቃልያ ውድድር እጣ ማውጣት ስነስርአት ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል፡፡ 9፡00 የጀመረው ፕሮግራምም እስከ 11፡30 ዘልቋል፡፡

በኘሮግራሙ መጀመርያ አቶ ሰሎሞን ገ/ሥላሴ የዕለቱን ስነ ሥርአት ቅደም ተከተል ካስተዋወቁ በኃላ የመክፈቻ ንግግር የተከበሩ አቶ ከማል ጀዋሮ ተደምጧል፡፡ ውድድሩን የምታስተናግደው ከተማም በሁሉም ረገድ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ከንቲባው ተናግረዋል፡፡ ለውድድሩ ተሳታፊዎችም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

በመቀጠል አጠቃላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ አባል እና የብሔራዊ ውድድር ኮሚቴ ሀላፊ አቶ አበበ ገላጋይ ውድድሩ የተሳካ እንዲሆን ስፖርት ፌዴሬሽኑ ልዩ ኮሚቴ አዋቅሮ ውድድሩን እንደሚመራው አስታውቀው ውድድሩ የተሳካ እዲሆን ተወዳዳሪ አካላት በስፖርታዊ ጨዋነት ውድድራቸው እንዲያካሄዱ አሳስበዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ታዳሚውን ባስደሰተ ንግግር 24ቱ ክለቦች ለከፍተኛው ብሄራዊ ሊግ ማለፋቸውን እንዳረጋገጡ አብስረዋል፡፡

11791900_941185265942160_3978013066769848469_o

በዳኝነቱ ዙርያ ንግግር ያደረጉት የኢትዮዽያ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢተርናሽናል አርቢቴር አቶ ልዑል ሰገድ በጋሻው በዳኝነቱ በኩል የተለየ ስራ አለመሰራቱን ነገር ግን ብሔራዊ ሊግ ዳኝተው የማያውቁ 12 ኢንተርናሽናል ዳኞችን የመደቡ ሲሆን ለዳኞቹም ከደቡብ አፍሪካና ከሱማልያ በመጡ ኢንስትራክቶች የብቃት ማሻሻያ ስልጠና ያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በውድድሩ ላይ ቅሬታዎች ቢከሰቱ በግልፅ በማቅረብ ሊፈታ እደንሚችም ገልፀዋል፡፡

የውድድሩ ስነ-ሥርአት ምን እንደሚመስል የገለፁት ደግሞ የውድድር ስነ ስራት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ገ/እግዚአብሔር ናቸው፡፡ አቶ ሰለሞን የውድድሩን ደንብ በዝርዝር የገለፁ ሲሆን ከየዞናቸው የመጡ ቡድኖች የመጀመርያው የምድብ ድልድል አንድ ላይ እንደማይደርሳቸው ተናግረዋል፡፡ የሜዳው ክፍፍልም በእጣ እንደሚወሰን አሳውቀዋል፡፡ የውድድሩ ሕገ ደንብ ለቡድኖች መበተኑ የተገለፀ ሲሆን በ2ኛ ሜዳነት የተያዘው ሳቢያን ሜዳ አመቺ አለመሆኑን በመግለፅ ክለቦች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ ይህም ረጅም ደቂዎች የፈጀ ክርክር አስተናግዷል፡፡

በመጨረሻም የምድብ ድልድሉ እጣ ማውጣት ስነስርአት የተካሄደ ሲሆን በ4 ምድቦች በእያንዳንዱ ምድብ 6 ቡድኖችን አቅፎ ይካሄዳል፡፡

የምድብ ድልድሉ ይህንን ይመስላል፡፡

ምድብ ሀ
ድሬዳዋ ከነማ
ፋሲል ከነማ
ወልዋሎ
አርሲ ነገሌ
ፌዴራል ፖሊስ
ቡራዩ ከነማ

ምድብ ለ
ባቱ ከነማ
ሱሉልታ ከነማ
ጅማ አባቡና
አዲስ አበባ አስተዳደር
ሻሸመኔ ከነማ
ናሽናል ሴሚንት

ምድብ ሐ
ጅማ ከነማ
መቀለ ከነማ
አላባ ከነማ
ሼር ኢትዮጵያ
ሰበታ ከነማ
ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ምድብ መ
ደቡብ ፖሊስ
ኢትዮጵያ መድን
አማራ ውሃ ስራ
የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት
ሆሳእና ከነማ
ወሎ ኮምቦልቻ

– ምድብ ሀ እና ለ የምድብ ጨዋታቸውን በሳቢያን ሜዳ ሲያደርጉ የምድብ ሐ እና መ ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታድየም ይካሄዳሉ

– ድሬዳዋ ከነማ ከአርሲ ነገሌ የሚደረገው የመክፈቻ ጨዋታ ነገ በድሬዳዋ ስታድየም ይደረጋል

– በሁለቱም ሜዳ በቀን 3 ጨዋታ ይደረጋል፡፡ ጠዋት 2፡00 ፣ 4፡00 እና 10፡00 ጨዋታዎቹ የሚደረጉበት ሰአት ናቸው፡፡

 

ዳንኤል መስፍን (ከድሬዳዋ)

ያጋሩ