የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሀምሌ 7 ልምምድ ይጀምራል

ኢትዮጵያ በ2015 በሞሮኮ ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የማጣርያ ጨዋታዋን ነሀሴ 29 ቀን 2006 አም. በአዲስ አበባ ስታድየም ከአልጄርያ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ትጀምራለች፡፡ ለጨዋታው 2 ወራት የቀሩት ሲሆን ብሄራዊ ቡድኑም ዝግጅቱን ከሀምሌ 7 ጀምሮ ያካሂዳል፡፡


አሰልጣኝ ማርያኖ ባሪቶ ባለፈው ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በቱርክ እና በሆላንድ ዝግጅት ለማድረግ እንዳሰቡ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን በመጀመርያ ከተመረጡት 38 ተጫዋቾች መካከል 7 ተጫዋቾችን ቀንሰው 1 ተጨማሪ ተጫዋች ከ20 አመት በታች ቡድኑ መርጠዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ታዳጊ ናትናኤል ዘለቀ በአዲሱ ምርጫ የተካተተ ሲሆን ዳዊት ፍቃዱ ፣ አሰግድ አክሊሉ ፣ ማታይ ሉል ፣ ታፈሰ ሰለሞን ፣ ሮቤል ግርማ ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና ሽመክት ጉግሳ ተቀንሰዋል፡፡

የ32ቱ ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው፡፡

ግብ ጠባቂዎች (3)

ጀማል ጣሰው (ቡና) ፣ ታሪኩ ጌትነት (ደደቢት) ፣ ሲሳይ ባንጫ (ደደቢት)

ተከላካዮች (10)

አሉላ ግርማ ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ ፣ ሳላዲን በርጊቾ ፣ አበባው ቡታቆ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ብርሃኑ ቦጋለ ፣ አክሊሉ አየነው ፣ ስዩም ተስፋዬ (ደደቢት) ፣ ቶክ ጄምስ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሽመልስ ተገኝ (መከላከያ) ፣ ግርማ በቀለ (ሀዋሳ ከነማ)

አማካዮች (14)

ምንያህል ተሸመ ፣ አዳነ ግርማ ፣ አንዳርጋቸው ረታ ፣ ናትናኤል ዘለቀ ፣ በኃይሉ አሰፋ ፣ ምንተስኖት አዳነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ አስቻለው ግርማ ፣ መስኡድ መሃመድ (ቡና) ፣ ታደለ መንገሻ (ደደቢት )፣ ሽመልስ በቀለ (ክለብ የለውም) ፣ አስራት መገርሳ (ዳሽን) ፣ አዲስ ህንፃ (አህሊ ሼንዲ)

አጥቂዎች (5)

ኡመድ ኡኩሪ ፣ ፍጹም ገብረማርያም (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሳላዲን ሰኢድ (ዋዲ ዴግላ) ፣ ጌታነህ ከበደ (ቢድቬትስ ዊትስ) ፣ ፍቅሩ ተፈራ (ክለብ የለውም)

ያጋሩ