ብሄራዊ ሊጉ ነገ በሚደረጉ 6 ጨዋታዎች ይቀጥላል

ትናንት የተጀመረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የምድብ ጨዋታ ነገ በሚደረጉ 6 ጨዋታ ይቀጥላል፡፡ ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው ጨዋታዎችም ይካሄዳሉ፡፡

በምድብ 2 የሚገኙት ክለቦች ነገ በሳቢያን ሜዳ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡ ጠዋት 3፡00 ላይ ናሽናል ሴሚንት ከጅማ አባቡና ጋር የእለቱን የመጀመርያ ጨዋታ ሲያደርጉ ቀጥሎ ደግሞ በ5፡00 ደግሞ ሻሸመኔ ከነማ ከሱሉልታ ከነማ ጋር ይፋለማሉ፡፡ አዲስ አበባ ከነማ ባቱ ከነማን የሚገጥምበት የምድቡ የእለቱ የመጨረሻ ጨዋታ 10፡00 ላይ ይካሄዳል፡፡

በምድብ 4 የሚደረገው ጨዋታ በድሬዳዋ ስታድየም ይካሄዳል፡፡ በ2007 የብሄራዊ ሊግ የዞኖች ውድድር ላይ በግሩም አቋም ምድባቸውን በበላይነት ያጠናቀቁት ደቡብ ፖሊስ እና መድን የምድቡን ትልቅ ጨዋታ ነገ በ4፡00 ይካሄዳል፡፡ የሁለቱን ጨዋታ ተከትሎ በ8፡00 የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ከ ወሎ ኮምቦልቻ ይፋለማሉ፡፡ በ10፡00 ደግሞ አማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (አውስኮድ) ከ ሆሳእና ከነማ ይጫወታሉ፡፡

(ዳንኤል መስፍን – ድሬዳዋ)

ያጋሩ