የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች አይናቸውን ብሄራዊ ሊጉ ላይ አሳርፈዋል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ተጫዋቾችን ለመመልመል ድሬዳዋ ከትመዋል፡፡ ትላንት እና ዛሬ የተደረጉትን ጨዋታዎችም ሲመለከቱ ታይተዋል፡፡ የሊጉ ክለቦች አሰልጣኞች ፣ ኃላፊዎች እና መልማዮችን ወደ ድሬዳዋ የላኩ ሲሆን አንዳንድ ክለቦችም ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከወዲሁ ከስምምነት እየደረሱ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

አምና በተመሳሳይ ከብሄራዊ ሊጉ ክለቦች ተጫዋቾችን ያስፈረሙት የመከላከያው አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ፣ ትኩረቱን በብሄራዊ ሊጉ ተጫዋቾች ላይ እንዳደረገ ያስታወቀው አርባምንጭ ከነማ መልማይ ፣ በርካታ ተጫዋቾቹን ያጡት የድቻው መሳይ ተፈሪ ፣ የኢትዮጵያ ቡናው ፖፓዲች ፣ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ዘሪሁን ሸንገታ ፣ የደቡብ ፖሊሱን ሚካኤል ለማን ያስፈረሙት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በድሬዳዋ ተገኝተው አዳዲስ ፊቶችን እየተከታተሉ ከሚገኙ አሰልጣኞች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ክለቦች ከብሄራዊ ሊግ የሚገኙ ተጫዋቾች ዋጋ በንፅፅር ከፕሪሚየር ሊጉ ተጫዋቾች አነስተኛ በመሆናቸው በቅርብ አመታት የተካሄዱ የብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድሮች ለፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች እደ አንድ የተጫዋች ምንጭ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

(ዳንኤል መስፍን – ድሬዳዋ)

ያጋሩ