ሁሉም የብሄራዊ ሊጉ ጨዋታዎች ወደ ዋናው ስታድየም ዞረዋል

የብሄራዊ ሊጉን ጨዋታዎች እንዲያስተናግድ ተመርጦ የነበረው ሳቢያን ሜዳ ከዚህ በኋላ ምንም አይነት ውድድር እንደማይካሄድበት የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

ትላንት በዚሁ ሜዳ ሊካሄዱ የነበሩት የምድብ ለ ጨዋታዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ለዛሬ ተላልፈው የነበረ ሲሆን ከዚህ በኋላ የሚደረጉ ጨዋታዎችም በዋናው ድሬዳዋ ስታድየም እንደሚደረጉ ኮሚቴው ጨምሮ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት የድሬዳዋ ስታድየም ከሐሙስ ጀምሮ በቀን 4 ጨዋታዎች የሚያስተናግድ ሲሆን የነገዎቹ የምድብ ሀ ጨዋታዎች በተያዘላቸው ፕሮግራም መሰረት ሲካሄዱ ሌሎቹ ጨዋታዎች ከሀሙስ ጀምሮ በሚወጣላቸው አዲስ ፕሮግራም መሰረት ይካሄዳሉ፡፡

4፡00 – ቡራዩ ከነማ ከ ድሬዳዋ ከነማ

8፡00 ፋሲል ከነማ ከ አርሰ ነገሌ

10፡00 ወልዋሎ ከፌዴራል ፖሊስ በድሬዳዋ ስታድየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡

የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴው እዳታስወቀው ውድድሩ ሙሉ ለሙሉ ድሬዳዋ ስታድየም ቢካሄድም በተያዘለት የጊዜ ገደብ ነሃሴ 17 ይጠናቀቃል፡፡

ሜዳው ኳስን በአግባቡ ለማንሸራሸር አስቸጋሪ ከመሆኑ በተጨማሪ በተጫዋቾች ላይም ከፍተኛ ጉዳቶች አስከትሏል፡፡

የሳቢያን ሜዳ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ መወሰኑ ቀድሞውንም በሜዳው ላይ ቅሬታ ሲያቀርቡ የነበሩትን ክለቦችንና ጉዳት እያስታገዱ የሚገኙ ተጫዋቾችን ያስደሰተ ውሳኔ ሆኗል፡፡

ያጋሩ