ታላቁ የጣሊያን ክለብ ኤሲ ሚላን ኢትዮጵያዊ ዝርያ ያለውን ሰይድ ያሲን የተባለ ተጫዋች ማስፈረሙን አስታውቋል። የ14 ዓመቱ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በጣሊያን ሶስተኛ ዲቪዝዮን ሲጫወት ለነበረው እና በአመቱ መጨረሻ ወደ ሴሪያ D ለወረደው ኖሰሪና ክለብ ሲጫወት የቆየ ሲሆን ናፖሊ እና ኢንተር ሚላንን ጨምሮ ከብዙ ክለቦች የዝውውር ጥያቄ ቢቀርብለትም ማረፍያው ሮሶነሪዎቹ ጋር ሆኗል።
ሰይድ የተወለደው ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን ገና በህፃንነቱ ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ጣሊያን ተጉዟል።
ወጣቱ አማካይ በቀጣዩ ዓመት Giovanissimi Nazionali በተባለው ውድድር የሚሳተፈው የሚላን ወጣት ቡድን አባል ይሆናል።