የሴካፋ የክለቦች ዋንጫ የምድብ ድልድል ወጣበሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ ስፖንሰር የተደረገው የ2014 የሴካፋ ክለቦች ዋንጫ (ካጋሜ ካፕ) ከነሃሴ 3 እስከ 17 በሩዋንዳ ይካሄዳል፡፡

ኢትዮጵን የሚወክለው ክለብም በ2012/13 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ያነሳው ደደቢት ይሆናል፡፡

12 ክለቦች የሚሳተፉበት ይህ ውድድር የምድብ ድልድል ዛሬ የወጣ ሲሆን የኢትዮጵያው ተወካይ ደደቢት በምድብ አንድ ተደልድሏል፡፡


የምድብ ድልድሉ ይህን ይመስላል፡-

ምድብ 1

ያንጋ አፍሪካ – ታንዛንያ

ደደቢት – ኢትዮጵያ

ራዮን ስፖርትስ – ሩዋንዳ

ኬኤምኬኤም – ዛንዚባር

ምድብ 2

ጎር ማሂያ – ኬንያ

ኤፒአር – ሩዋንዳ

ካምፓላ ሲቲ – ዩጋንዳ

ኤኤስኤስ – ጅቡቲ

ምድብ 3

ቪታል ኦ – ብሩንዲ

አል ሜሪክ – ሱዳን

ፍላምቤዉ ዴል ኤስት (ብሩንዲ)

ባንዳዲር – ሶማልያ

-ውድድሩ ነሃሴ 3 ቀን 2006 በሩዋንዳ ኪጋሊ የሚከፈት ሲሆን ያለፈው የውድድር ዘመን በብሩንዲው ቪታል ኦ አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

– በአንድ ምድብ የተደለደሉት ደደቢት እና የዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም በዚህ አመት በቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣር መጫወታቸው ይታወሳል፡፡

– ደደቢት በሴካፋ ውድድሮች ሲካፈል ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡

ሩዋንዳ በአዘጋጅነቷ፣ ብሩንዲ ደግሞ አምና ውድድሩን ያሸነፈው ቪታሎ ክለብ ሃገር በመሆኗ እያንዳንዳቸው ሁለት ክለብ የሚያሳትፉ ሲሆን ሌሎች የሴካፋ ሃገራት አንድ አንድ ተወካይ ይኖራቸዋል።

ያጋሩ