ደደቢት የጋብሬኤል “ሻይቡ” አህመድ ምትክን እየፈለገ ነው

ከሳምንት በፊት በደደቢት የነበረው ውል ከተጠናቀቀ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባልተገለፀ ዋጋ የተዛወረውን ጋናዊን የአማካይ ተከላካይ ጋብሬኤል ሻይቡ አህመድ ምትክ ተጫዋች ለማስፈረም ደደቢት ጥረት ጀምሯል፡፡ ስሙ ከደደቢት ጋር በከፍተኛ ደረጃ ሲያያዝ የነበረው አስራት መገርሳ የሻይቡ ምትክ ለማድረግ የታሰበው ዕውን ሳይሆን ቀርቷል፡፡ አስራት በዳሽን ቢራ ውሉን ማራዘሙ ሰማያዊ ጦሮቹን ሌላ አማራጮችን እንዲመለከቱ አስገድዷል፡፡

የሻይቡ ምትክን ለማግኘት ክለቡ ወደ ውጪ መመልከቱ አይቀሬ ነው፡፡ ክለቡ ተጫዋች ከውጪ ማስመጣት የሚፈልግ ሲሆን ድሬዳዋ ላይ በመካሄድ ላይ ባለው የብሄራዊ ሊጉ የማጠቃለያ ውድድር ላይ መልማዮቹን ልኮ ተጫዋቾችን በመመልከት ላይ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *