ኢትዮጵያ ቡና ከቶጎ እና ቤኒን ተጫዋቾች ሊያስመጣ ነው

አትዮጵያ ቡና ከምዕራብ አፍሪካ ግብ ጠባቂ፣ አማካይ እና አጥቂ ሊያስመጣ ነው፡፡ ተጫዋቾቹ ከቶጎ እና ቤኒን እንደሆኑ ማወቅ ተችሏል፡፡ በክለቡ የሙከራ ጊዜ የሚያሳልፉት ተጫዋቾቹ በሙከራ ግዜያቸው ከተሳካ ክለቡን ለ2008 የውድድር ዓመት የሚቀላቀሉ ይሆናሉ፡፡

አዲሱ የተጫዋቾች ዝውውር ደንብ መሰረት አንድ ክለብ 3 የውጪ ሃገር ተጫዋቾችን መያዝ አለበት ለዚህም የኢትዮጵያ ቡና በክለቡ ከነበሩት 4 የውጪ ሃገር ተጫዋቾችን መካከል ቤኒንያዊው አቢኪዩ ሻኪሩ ብቻ በክለቡ ቀርቷል፡፡ ቡና አምና ያስፈረማቸው ካሜሮናዊ ተከላካይ ኦሊቨር ዋረን የአንድ ዓመት ውሉ በመጠናቀቁ፣ ቶጎዋዊው ኤዶም ሆሶሮቪ የ3 ዓመት ውል ፈርሞ የነበረ ቢሆንም ውሉ ፈርሶ ዳሽን ቢራን ተቀላቅሏል እንዲሁም ናይጄሪያዊው ግብ ጠባቂ ፊበርሲማ ኔልሰን ከክለቡ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ከክለቡ የተለያዩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ባደረሰን መረጃ መሰረት አዲሱ ግብ ጠባቂ እና ተከላካዩ ለክለቡ የሚፈርሙበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ በተለይ ክለቡ በግብ ጠባቂ ስፍራ ላይ ጌቱ ተስፋዬ ብቻ ስላለው ግብ ጠባቂ ማስፈረሙ አይቀሬ ነው፡፡ የሃዋሳ ከነማውን ተከላካይ ግርማ በቀለን ለማስፈረም ያደረገው ጥረት ያልተሳካው ቡና ተከላካይ ማስመጣቱን እንደመፍትሄ ወስዶታል፡፡ የሚመጣው አጥቂ ከአብኪዩ ሻኪሩ ጋር በሙከራ ግዜው የሚያሳልፍ ሲሆን አሰልጣኝ ድራጋን ፓፓዲችን ማሳመን የሚችለው አጥቂ በክለቡ ይቆያል፡፡ ይህም ከቡና ጋር ቀሪ የ2 ዓመት ውል የሚቀረው ሻኪሩ በክለቡ የሚኖረውን ቆይታ አጠራጣሪ ያደርገዋል፡፡ ሻኪሩ በተለያዩ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ይፈለጋል፡፡ ሻኪሩን በውሰት መውሰድ የሚፈልጉ የፕሪምየር ሊግ ክለቦችም አሉ፡፡ ሻኪሩ ለዕረፍት የትውልድ ሃገሩ በሆነችው ናይጄሪያ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *