የፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ የ6 ተጫዋቾቹን ኮንትራት ለተጨማሪ 2 አመታት ማራዘሙን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ክለቡ ውላቸውን ያደሰላቸው ተጫዋች አምበሉ ደጉ ደበበ ፣ የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች በኃይሉ አሰፋ ፣ አማካዮቹ ናትናኤል ዘለቀ ፣ ተስፋዬ አለባቸው እና ምንያህል ተሾመ እንዲሁም ተከላካዩ አለማየሁ ሙለታ ናቸው፡፡
ክለቡ የተጫዋቾቹን ውል ማደሱን ከመጥቀስ ውጪ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚከፈላቸው ከመግለፅ ተቆጥቧል፡፡