የቅዱስ ጊዮርጊስ የዝውውር ወሬዎች


— ቅዱስ ጊዮርጊስ የንግድ ባንኩ መሃሪ መናን ዝውውር መጨረሱ ተወርቷል፡፡ የኢትዮጰያ ንግድ ባንኩ የግራ መስመር ተከላካይከ ሃምራዊዎቹ ጋር ድንቅ የውድድር ዘመን ያሳለፈ ሲሆን ኮንትራቱ በመጠናቀቁ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ሲነሳ ቆይቷል፡፡

— ፈረሰኞቹ ከመሃሪ በተጨማሪ የፋሲካ ዝውውርን መጨረሳቸው እየተነገረ ነው፡፡ አማካዩ ከኢትዮጰያ ቡና ጋር ያለውን ውል አፍርሶ ክለቡን የለቀቀ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስን የመቀላቀል እድሉ ሰፊ ነው፡፡

— የሊጉ ቻምፒዮን የካሜሩናዊው ዊልያም ኤሳድጆ እና ምንተስኖት አዳነን ኮንትራት ለማራዘም ከጫፍ ደርሷል፡፡

— ቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞ ተጫዋቹን ለመመለስ ፍላጎት አለው፡፡ የንግድ ባንኩ የአጥቂ አማካይ ኤልያስ ማሞ ከክለቡ ጋር ያለው ኮንትራት በመጠናቀቁና ክለቡም በቦታው ሌሎች ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ላይ በመሆኑ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊያመራ ይችላል፡፡

— ሙሉውን የውድድር ዘመን በጉዳት ያሳለፈው ዮናታን ብርሃኔ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሊለቅ ይችላል፡፡ ዮናታን ዘንድሮ ለፈረሰኞቹ የተሰለፈው በወዳጅነት ጨዋታዎች እና ከሙገር ጋር በተደረገው የኢትዮጰያ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ብቻ ነው፡፡

ምንጭ – ፕላኔት ስፖርት (ኤፍኤም 96.3)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *