የኢትዮጵያ ቡና የዝውውር ወሬዎች

ኢትዮጵያ ቡና የአምበሉ ዳዊት እስጢፋኖስን ኮንትራት አራዝሟል፡፡ ክለቡ ውሉ የተጠናቀቀውን ተጫዋች ኮንትራት ለማራዘም ከ900ሺህ እስከ 1 ሚልዮን ብር ወጪ እንዳደረገ ተወርቷል፡፡

— ቡና ከዳዊት እስጢፋኖስ በተጨማሪ የቶክ ጄምስ ፣ ጀማል ጣሰው ፣ መስኡድ መሃመድ እና ጋቶች ፓኖምን ኮንትራት ያራዘመ ሲሆን የአዲስ አበባ ከነማውን አማካይ ሚኪያስ በየነን ዝውውር አጠናቋል፡፡

— ፋሲካ አስፋውን ያጣው ኢትዮጰያ ቡና አማካዩን ለመተካት ፊቱን ወደ ሙገሩ አምበል በኃይሉ ግርማ እና የመከላከያው ተክለ ወልድ ፍቃዱ አዙሯል፡፡

— በተያያዘ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በጥቂት ጨዋታዎች የመሰለፍ እድል የተሰጠው ኤፍሬም ዘካርያስ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

-ምንጭ – ፕላኔት ስፖርት (ኤፍኤም 96.3)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *