በተከታታይ 4 ጨዋታዎች ከድል የራቀው ሀዋሳ ከተማ ለአምስት የቡድኑ ተጫዋቾች አቋማቸውን እንዲያሻሽሉ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መስጠቱን ለሶከር ኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡
ክለቡ ለተጫዋቾቹ በሰጠው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጫዋቾቹ በሜዳ ላይ አቋማቸው በመውረዱ በቀጣይ እንዲያሻሽሉ እና ክለቡን በሚፈለገው መልኩ በቀጣይ ጊዜያት ለማገልገል ጥረት አንዲያደርጉ ፤ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ክለቡ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡ ሀዋሳ ከተማ ግልባጭ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማስገባቱን ከመግለፅ ውጪ የተጫዋቹን ማንነት ለሶከር ኢትዮጵያ ከመናገር ተቆጥቧል፡፡
በተያያዘ ዜና አርባምንጭ ከተማ በውድድር አመቱ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች መካከል ለጋናዊው ተከላካይ ኤክስ አሙዙ በተደጋጋሚ ‹‹አሞኛል›› በሚል ሰበብ ልምምድ በመቅረት እና አቋም መውረድ ምክንያት ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ታውቋል፡፡