በ5 ምድቦች ከ60 ክለቦች በላይ እየተሳተፉበት የሚገኘው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ከ5 ሳምንታት በላይ ቢጓዝም የምድብ ሐ ጨዋታዎች በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት እስካሁን ሳይካሄዱ ቆይተዋል፡፡
ከሌሎች ምድቦች ጋር በእኩል ፍጥነት መሔድ ያልቻለው የምድብ ሐ አማራ ፖሊስ ከ መርሳ ሀርቡ ካደረጉት ጨዋታ በቀር እስካሁን ጨዋታ ያልተደረገበት ሲሆን ከፌዴሬሽኑ ባገኘነው መረጃ መሰረት ከጥር 27 ጀምሮ በ3 ምድቦች ተከፍሎ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የየምድቦቹ ጨዋታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ በቀዳሚነት የሚያጠናቅቁ ክለቦች ወደ ማጠቃለያ ውድድር በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል፡፡
ምድብ ሐ – 1
ሰሎዳ አድዋ፣ ትግራይ ውሃ ስራ፣ ራያ አዘቦ፣ ትግራይ ዋልታ ፖሊስ
ምድብ ሐ – 2
ደባርቅ ከተማ ፣ ዳባት ከተማ ፣ አምባ ጊዮርጊስ ፣ አማራ ፖሊስ
ምድብ ሐ – 3
የጁ ፍሬ ወልዲያ ፣ መርሳ ከተማ ፣ ዳሞት ከተማ ፣ ላስታ ላሊበላ ፣ አዊ አምፒልታቅ
የአንደኛ ሊግ የሌሎች ምድቦችን መርሃ ግብሮች እና የደረጃ ሰንጠረዥ ሊንኩን በመጫን ያገኛሉ || አንደኛ ሊግ