ወደ ብሄራዊ ሊጉ ለመግባት የሚደረገው ውድድር በጅግጅጋ ይካሄዳል

 

በ2008 የውድድር ዘመን በብሄራዊ ሊግ (ከፕሪሚየር ሊግ እና ሱፐር ሊግ ቀጥሎ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሊግ) ለመሳተፍ የሚደረገው የክልል ክለቦች ቻምፒዮና የማጠቃለያ ውድድር በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ዛሬ ይጀመራል፡፡

በውድድሩ ላይ ከአፋር ክልል በስተቀር ከሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች የውስጥ ውድድሮች የተውጣጡ 35 ክለቦች በ6 ምድቦች የተከፈሉ ሲሆን ለ3 ሳምንት በሚቆየው ውድድር የሩብ ፍፃሜውን የሚቀላቀሉ 8 ክለቦች ወደ ብሄራዊ ሊጉ ያልፋሉ፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው ለውድድሩ 24 ዳኞች እና 9 ኮሚሽነሮች የተመደቡ ሲሆን ውድድሩን በብቃት ለመምራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ይህ ውድድር በ3 ሜዳዎች የሚካሄድ ሲሆን የጅግጅጋ ስታድየም ፣ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና የጅግጅጋ መምህራን ኮሌጅ ሜዳዎች የውድድሩ ቦታዎች ናቸው፡፡

የእጣ ማውጣት ስነስርአት Photo © EFF PR
የእጣ ማውጣት ስነስርአት Photo © EFF PR

ትላንት የወጣው የምድብ ድልድል ይህንን ይመስላል፡-

ምድብ 1 – ኮረም(ትግራይ) ፣ አምቦ ከነማ(ኦሮምያ) ፣ ሐረር ጃኔላ (ሐረሪ) ፣ ጂግጂጋ ማዘጋጃ (ሶማሌ) ፣ ወላይታ ሶዶ (ደቡብ) ፣ ቂርቆስ (አአ)

ምድብ 2 – ሐረር ሸንኮር (ሐረሪ) ፣ ሐረር ቡና (ድሬዳዋ) ፣ ኬ.ኤስ.ኤስ.ኤ(አአ) ፣ ብርሃን (ቤኒሻንጉል) ፣ ጣና ባህርዳር (አማራ) ፣ አሰላ ከነማ (ኦሮምያ)

ምድብ 3 – ገላን (ኦሮምያ) ፣ አባይ ሻንኮሌ (ቤኒሻንጉል) ፣ ቡሬ ከነማ (አማራ) ፣ ካራማራ (ሱማሌ) ጉለሌ (አአ) ዱራሜ (ደቡብ)

ምድብ 4 – አዲስ አበባ ራዕይ (አአ) ፣ ሃብኮን (ትግራይ) ፣ አሊ ሐብቴ ጋራዥ (ድሬዳዋ) ፣ ገንዳውሃ (አማራ) ፣ ሐረር ማረምያ (ሐረሪ) ፣ ጋምቤላ ዩኒቲ (ጋምቤላ)

ምድብ 5 – ልዩ ፖሊስ (ሶማሌ) ፣ ላሊበላ (አማራ) ፣ ፍራውን ከነማ(ትግራይ) ፣ አፍረን ቀሎ (ድሬዳዋ) ፣ አስሚድ(ደቡብ)

ምድብ 6 – ቤኒሻንጉል ፖሊስ (ቤኒሻንጉል) ፣ ውቅሮ ከነማ (ትግራይ) ፣ ቱሉ ቦሎ(ኦሮምያ) ፣ ደባርቅ (አማራ) ፣ ሃፍን (ሱማሌ) ፣ ዋልያ (ድሬዳዋ)

ውድድሩ የአስተናጋጇ ክልል ክለብ የሆነው ጅግጅጋ ማዘጋጃ ከ ሀረሪው ጂኔላ በ9፡00 በሚያደርጉት ጨዋታ ይከፈታል፡፡

 

ያጋሩ