የክልል ክለቦች ቻምፒዮንሺፕ ትላንት ተጀምሯል

በ2008 ውድድር ዘመን ወደሚደረገው ብሄራዊ ሊግ ለመግባት የሚደረገው ውድድር ትላንት በይፋ ተከፍቷል፡፡ 35 ክለቦችን በ6 ምድቦች አቅፎ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ይህ ውድድር የእገርኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ በተገኙበት በጅግጅጋ ከተማ ተከፍቷል፡፡

በመክፈቻው የተገናኙት የሶማሌ ክልሉ ጅግጅጋ ማዘጋጃ ቤት እና የሐረሪው ጃኒላ ሲሆኑ ጂኒላ 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ትላንት በተካሄዱ ሌሎች የምድብ ሀ ጨዋታዎችም ወላይታ ሶዶ አምቦ ከተማን በተመሳሳይ 1-0 ሲያሸንፍ የአዲስ አበባው ቂርቆስ ክ/ከተማ ከትግራዩ ኮረም 0-0 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ትላንት በተካሄዱ ሌሎች የምድብ ሀ ጨዋታዎችም ወላይታ ሶዶ አምቦ ከተማን በተመሳሳይ 1-0 ሲያሸንፍ የአዲስ አበባው ቂርቆስ ክ/ከተማ ከትግራዩ ኮረም 0-0 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

1
የኢእፌ አመራሮች በመክፈቻው ስነስርአት ላይ ፎቶ © EFF PR

 

ውድድሩ ለ3 ሳምንታት የሚቀጥል ሲሆን ሩብ ፍፃሜውን የሚቀላቀሉ 8 ክለቦች ለ2008 ብሄራዊ ሊግ ውድድር ያልፋሉ፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ የውድድሩን ውጤቶች እና ዘገባዎች ለማድረስ ጥረት ታደርጋለች፡፡ ( የውድድሩን የደረጃ ሰንጠረዥ እና ውጤቶች ለማወቅ ሜኑ ላይ Competitions ቀጥሎም ከሚመጡት አማራጮች Regional Championship የሚለውን ተጭነው ያገኙታል፡፡)

 

ያጋሩ