“ብዙ ሰዎች ከመጣንበት ዞን አኳያ አይተውን ዝቅተኛ ግምት ሰጥተውን ነበር” ባሪ ለዱም

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ለወልቂጤ ከነማ ተጫውቷል ናይጄሪዊው የፊት መስመር ተሰላፊ አሁን ለጅማ አባ ቡና እየተጫወተ ይገኛል ባሪ ለዱም፡፡ ከናይጄሪያ ሪቨርስ ክፍለ ግዛት ፖርት ሃርኮት ከተማ የተገኘው ባሪ ያለውን ልምድ ተጠቅሞ ጅማ አባ ቡና ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ከፍተኛ ትግል እንደሚያደርግ ይናገራል፡፡ ባሪ ለጅማ አባ ቡና አሁን በመደረግ ላይ ባለው የብሄራዊ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ባቱ ከነማ ላይ እና ሻሸመኔ ከነማ ላይ ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡ ጅማ አባ ቡና በምድብ ለ ከአዲስ አበባ ከተማ፣ ሻሸመኔ ከነማ፣ ባቱ ከነማ፣ ናሽናል ሲሜንት እና ሱሉልታ ከነማ ጋር መደልደሉ ይታወሳል፡፡ ካደረጓቸው 3 ጨዋታዎችም 7 ነጥብ በመያዝ ምድቡን ይመራል፡፡
ብሄራዊ ሊጉን በተመለከተ ሶከር ኢትዮጵያ ከባሪ ለዱም ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡

ስለምድብ ጨዋታዎች
የምድብ ጨዋታዎች በጣም ፉክክር ይበዛባቸውል፡፡ በምድብ ውስጥ ያሉት ክለቦች ለማሸነፍ ቀላል አይደለም፡፡ ሁሉም ክለቦች ያለቸውን አውጥተው ስለሚጫወቱ ጨዋታዎች በጣም ከባድ ናቸው፡፡ ሁሉም ያላቸውን ጥሩ ብቃት ማሳየት ይፈልጋሉ፡፡ ይህም ያልተጠበቀ ውጤት እንዲመዘገብ እንዲሁም ወደ ፕሪምየር ሊግ የሚያድጉት ክለቦች ማንነትን ለመገመት አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ ጨዋታዎችም ከፍተኛ ትግል ስለሚደረግባቸው ጨዋታዎች ከባድ ናቸው፡፡

 

ስለጅማ አባ ቡና የእስካሁን ስኬት

ብዙ ሰዎች ከመጣንበት ዞን አኳያ አይተውን ዝቅተኛ ግምት ሰጥተውን ነበር፡፡ ይህም ያለ ጫና እንድንጫወት እረድቶናል፡፡ በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ ተጋጣሚያችንን እንደምናሸንፍ አምነን ነው ወደ ሜዳ የምንገባው፡፡ የምንጫወተው በቡድን ነው፡፡ አንዳችን ለአንዳችን እገዛ እናደርጋለን፡፡ በጣም ጥሩ አሰልጣኝ (የጅማ አባ ቡና ዋና አሰልጣኝ ደረጄ) አለን አንዳንድ ግዜ እኔ የማይስማሙኝ ውሳኔዎች ቢያሳልፍም አሁንም ድረስ ጎበዝ እና አሸናፊ አሰልጣኝ አለን፡፡ የአካል ብቃታችን በብዙ መልኩ ጠንካራ ጎናችን ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህም ለስኬታችን ዋነኛ ሚስጥር ነው፡፡

 

22823_10205972301699658_1374400205382784718_n

ከፕርምየር ሊግ ክለቦች የመጣ የዝውውር ጥያቄ
እኔ አሁን ሙሉ ለሙሉ ትኩረቴ ቡድኔን መርዳት ላይ ነው፡፡ አሰልጣኜ የተወሰኑ የፕሪምየር ሊግ ክለቦችን የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ስለኔ እንዳናገሩት ነግሮኛል፡፡ ነገር ግን የትኞቹ ክለቦች እንደፈለጉኝ ግን ከመናገር ተቆጥቧል፡፡

ወደፕሪምየር ሊግ የማለፍ ተስፋ
ካመንክ የማይቻል ነገር የለም፡፡ በቡድናችን ካምፕ ውስጥ ያለው መንፈስ ጥሩ ነው፡፡ የአሸናፊነት መንፈሳችንም ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ ነው፡፡ ግን ነገሮችን ቀስ በቀስ እያስኬድን ነው፡፡

ስለከተማ ተቀናቃኝ ክለብ ጅማ ከነማ
ጥሩ ቡድን አላቸው፡፡ የአጨዋወት ፍልስፍናቸው ይማርከኛል፡፡

 

ስለድሬዳዋ እና ስለደጋፊዎች
ድሬዳዋ በጣም ትሞቃለች፡፡ እንደምጥጠብቀው ስቴዲየሙ ሞልቶ አታይም፡፡ ስታዲየሙ አብዛኛውን ግዜ በከፊል ነው የሚሞላው፡፡ ደጋፊዎቹ ለክለቦቻቸው ያላቸው ፍቅር እና ድጋፍ በጣም ይለያል፡፡ እኛም የተወሰኑ ደጋፊዎችን ማግኘት ችለናል፡፡ ሁለት የቡድን አጋሮቼ የድሬዳዋ ተወላጅ ናቸው፡፡ በነሱ ምክንያት ደጋፈዎችን ማግኘት ችለናል፡፡

ያጋሩ