የወዳጅነት ጨዋታው ጉዳይ ግርታን ፈጥሯል

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በነሃሴ ወር መጨረሻ ከሲሸልስ ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ዝግጅት ማድረግ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ለዝግጅቱ ይረዳውም ዘንድ ከዩጋንዳ አልያም ሩዋንዳ ጋር የዝግጅት ጨዋታ ለማድረግ ለፌዴሬሽኖቹ ጥያቄዎችን አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የወዳጅነት ጨዋታውን ለማድረግ ለሁለቱም ሃገራት ደብዳቤ ያስገባ ሲሆን የሁለቱም የጨዋታ ቀን ኦገስት 28 መሆኑ ግን ግርታን ፈጥሯል፡፡

የዩጋንዳው አሰልጣኝ ስሬድየቪች ሚሉቲን ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከሩዋንዳ እና ዩጋንዳ ጋር በተመሳሳይ ቀን ለመጫወት ደብዳቤ መላኩ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ከሁለቱም ጋር ለመጫወት ጥያቄ ያቀረቡት በተመሳሳይ ቀን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ግርታን ፈጥሮብናል፡፡ ለፌዴሬሽኑ ጥርት ያለ ምላሽ እዲሰጠን ጥያቄ አቅርበናል፡፡ ምናልባት ከፌዴሬሽኖቹ ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት Misunderstand ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል፡፡ ›› ብለዋል፡፡

‹‹ ሚቾ › አያይዘውም ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር በአበበ ቢቂላ ስታድየም የዝግጅት ጨዋታውን ቢያደርጉ ለሁለቱም ቡድኖች ጠቃሚ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

‹‹ ፍላጎታችን አበበ ቢቂላ ላይ መጫወት ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ ከኮሞሮስ ጋር የምናደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ የሚካሄደው በሰው ሰራሽ ሜዳ ነው፡፡ ዋልያዎቹም በተመሳሳይ በሲሸልስ በሰው ሰራሽ ሜዳ ይጫወታሉ፡፡ ስለዚህ ለሁለታችንም ጥሩ ዝግጅት እንድናደርግ ይረዳናል፡፡ ›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ህዝብ ግንኙነት በጉዳዩ ላይ በሰጠው ምላሽ ደግሞ ለሁለቱም ጥያቄ ያቀረቡት የተሸለውን ለመምረጥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

‹‹ ለሀለቱም ቡድኖች ኦገስት 28 ለመጫወት ጥያቄ አቅርበናል፡፡ በመጨረሻም ሰምምነት ላይ ከደረስነው እና ለኛ ጥቅም ይሰጣል ብለን ያሰብነውን ጨዋታ እናደርጋለን፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ ከሩዋንዳ ጋር የተሻለ መቀራረብ በመፍጠራችን ከሩዋንዳ ጋር ጨዋታ ልናደርግ እንችላለን፡፡ ››

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *