ጌታነህ ከበደ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ?
የቢድቬትስ ዊትሱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ወደ ኢትዮጰያ ሊመለስ ይችላል የሚሉ ጭምጭምታዎች እየተናፈሱ ነው፡፡ ይህን ተከትሎም የአዲስ አበባ ክለቦች ተጫዋቹን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል ተብሏል፡፡ የ2005 የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ በቀድሞ ክለቡ ደደቢት ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚፈለግ ሲሆን በቢድቬትስ ዊትስ ያለውን ኮንትራት ለ1 ተጨማሪ የውድድር ዘመን እንዳራዘመም እየተወራ ነው፡፡
ለተጫዋቹ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚገልፁት ተጫዋቹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለመስማማት ጫፍ እንደደረሰ ቢጠቁሙም ተጫዋቹ ከደቡብ አፍሪካ ለእረፍት ሲመለስ ከክለቡ ጋር ያለውን ውል አራዝሞ መምጣቱ ተወርቷል፡፡ ‹‹ ቅዱስ ጊዮርጊስ መጫወት ብፈልግም በቢድቬትስ ውሌን አራዝሜያለው ›› ማለቱ ተሰምቷል፡፡
ጌታነህ ከበደ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን አመዛኝ ጨዋታዎች በቢድቬትስ ዊትስ ተጠባባቂ ወንበር ላይ አሳልፎ አጠናቋል፡፡
.
ምንጭ – ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ (ሬድዮ)
ተዛማጅ ፅሁፎች
ሀዲያ ሆሳዕና የዕግድ ውሳኔ ተላለፈበት
ሀዲያ ሆሳዕና ከዚህ ቀደም በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የተሰጠበትን ውሳኔ ተግባራዊ አላደረገም በሚል የዕግድ ውሳኔ ተላልፎበታል። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ለ15 ተጫዋቾች...
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ወሳኝ ድል አሳክተዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተደረጉ አራት መርሐግብሮች ጅምሩን ሲያደርግ መከላከያ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ተጋጣሚዎቻቸውን...
የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 1-1 ድሬዳዋ ከተማ
በሊጉ ለመቆየት ብርቱ ትግል ተደርጎበት ነጥብ በመጋራት ከተጠናቀቀው ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ አሰልጣኞች የድህረ-ጨዋታ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ - አዳማ...
ከ17 እና ከ15 ዓመት በታች ውድድሮች የሚደረጉበት ቦታ እና ቀን ይፋ ሆኗል
የ2014 ከ17 ዓመት በታች እና ከ15 ዓመት በታች የፓይለት ፕሮጀክት ውድድሮች የሚደረጉበት ከተማ እና ቀን ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን...
የአሰልጣኞች አስተያየት | አርባምንጭ ከተማ 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰዓታት በፊት የተነጠቀውን የደረጃ ሰንጠረዥ አናትን መልሶ መረከቡን ካረጋገጠበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞች ድህረ ጨዋታ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኝ...
ሪፖርት | ፈረሰኞቹ መሪነታቸውን አስመልሰዋል
በከነዓን ማርክነህ ብቸኛ ግብ አርባምንጭ ከተማን የረታው ቅዱስ ጊዮርጊስ የአንደኝነት ደረጃውን ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ከፋሲል ከነማ መልሶ ተረክቧል። አርባምንጭ ከተማ...