በጋና አስተናጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በመጋቢት ወር ከሊቢያ ጋር ለሚያርገው የመጀመርያ ዙር የማጣርያ ጨዋታ ዝግጅት አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ 36 ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አድርጋለች። አሰልጣኝ ሰላም ይፋ ባደረገችው ዝርዝር ውስጥ ገሚሱ ለመጀመርያ ጊዜ ጥሪ የቀረበላቸው ሲሆን 11 ተጫዋቾች ከ17 አመት በታች ቡድን ፣ 8 ተጫዋቾች ደግሞ በ20 አመት በታች ቡድን የነበሩ ናቸው።
የተጫዋቾች ዝርዝር
ግብ ጠባቂዎች
ማርታ በቀለ (መከላከያ) ፣ አባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ገነት አክሊሉ (ደደቢት) ፣ ንግስት አበራ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሽብሬ ካንኮ (ኢትዮጵያ ቡና)
ተከላካዮች
መሠሉ አበራ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ፀጋነሽ ተሾመ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ፅዮን እስጢፋኖስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ዘለቃ አሰፋ (ደደቢት) ፣ ብዙአየሁ ታደሰ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ቤተልሄም ከፍያለው (ኤሌክትሪክ) ፣ መስከረም ካንኮ (ደደቢት) ፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ እፀገነት ብዙነህ (ደደቢት) ፣ ገነሜ ወርቁ (ጌዴኦ ዲላ)
አማካዮች
ሠናይት ቦጋለ (ደደቢት) ፣ አረጋሽ ልኬሳ (አካዳሚ) ፣ ዙሌይካ ጁሀድ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ቤዛዊት ተስፋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ህይወት ደንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ) ፣ ብሩክታዊት ግርማ (ደደቢት) ፣ ሜላት ደመቀ (አአ ከተማ) ፣ አለምነሽ ገረመው (ኤሌክትሪክ) ፣ መዲና ጀማል (ጥረት)
አጥቂዎች
ፎዚያ መሐመድ (አካዳሚ) ፣ ምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ቤተልሄም ሰማን (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሎዛ አበራ (ደደቢት) ፣ ትዕግስት ዘውዴ (ደደቢት) ፣ ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ) ፣ ረሂማ ዘርጋ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ልደት ተሎአ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ሰርካዲስ ጉታ (አዳማ ከተማ) ፣ ትዝታ ፈጠነ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ሲሳይ ገብረወልድ (አካዳሚ)
ሉሲዎቹ ዝግጅታቸውን የካቲት 27 የሚጀምሩ ሲሆን የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታቸውን ከሊቢያ ጋር ከሜዳቸው ውጪ ከመጋቢት 22 እስከ 24 ባሉት ቀናት ያደርጋሉ። የመልሱን ጨዋታ አአ ላይ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሲያደርጉ ይህን ዙር ካለፉም በቀጣይ የማጣርያ ዙር የሴኔጋል እና አልጄርያ አሸናፊን የሚገጥሙ ይሆናል።