መብራት ኃይል 3 ተጫዋቾችን አስፈረመ

መብራት ኃይል በበርካታ ክለቦች ሲፈለጉ የቆዩትን ሶስት ተጫዋቾች ማስፈረሙን ፕላኔት ስፖርት ዘግቧል፡፡

ቀዮቹ ያስፈረሟቸው ተጫዋቾች ወንድሜነህ ዘሪሁን ከ ሀዋሳ ከነማ ፣ ማናዬ ፋንቱን ከ መከላከያ እና አሰግድ አክሊሉ ከ ሙገር ሲሆኑ የተጫዋቾችን ኮንታረትም ለማራዘም እየጣረ መሆኑ ተወርቷል፡፡

ወንድሜነህ ዘሪሁን በኢትዮጵያ እግርኳስ በክህሎት ደረጃቸው ላቅ ያሉ ጨዋታ አቀጣጤች አንዱ ሲሆን ወደ ንግድ ባንክ ያመራው አብዱል ከሪም ሀሰንን ይተካል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ‹‹ ኦኬ ›› በሚለው ቅፅል ስሙ የሚታወቀው ወንድሜነህ ዘሪሁን እውቅናን ያገኘው በሙገር ሲሚንቶ ማልያ ነው፡፡ በአሰላው ክለብ ባሳየው አቋም ወደ መከላከያ ተዘዋውሮ 2 የውድድር ዘመናትን በቀይ እና አረንጓዴው ማልያ አሳልፏል፡፡ በ2004 ደግሞ የደቡቡን ክለብ ሀዋሳ ከነማ ተቀላቅሎ እስከ ዘንድሮው የውድድር ዘመን መጨረሻ ድረስ ቆይቷል፡፡

ማናዬ ፋንቱ በኢትዮጵያ እግርኳስ ተስፋ ከተጣለባቸው አጥቂዎች አንዱ ነው፡፡ በቻን ቻምፒዮን-ሺፕ ላይ የተካፈለው ማናዬ ፋንቱ መብራት ኃይል 3ኛ ክለቡ ነው፡፡ ወደ መከላከያ ከማምራቱ በፊት ለደቡብ ፖሊስ ተቻውቷል፡፡

አሰግድ አክሊሉ ወደፊት ታላቅ ግብ ጠባቂ እንደሚሆን ተስፋ የተጣለበት ተጫዋች ነው፡፡ ዘንድሮ በሙገር ሲሚንቶ እና በአፍሪካ ከ20 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ባሳየው ብቃት በበርካቶች አድናቆት ተችሮታል፡፡

መብራት ኃይል ከሶስቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንደሚለቁ የሚጠበቁት ዊልያም ኤሳድጆ እና ዘካርያስ ቱጂን ለማስፈረም እየጣረ ሲሆን የበረከት ይስሃቅ እና አልሳዲቅ አልማሃን ኮንትራት ለማራዘም እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡

ያጋሩ