ወልዲያ ወደ ክለቡ ሳይመለሱ በቆዩት ፍፁም ገብረ ማርያም ፣ ታደለ ምህረቴ እና ያሬድ ብርሀኑ ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።
ክለቡ በሊጉ 12ኛ ሳምንት ጅማ ላይ በጅማ አባ ጅፋር ሽንፈት ካስተናገደ በኃላ በወቅቱ በተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት ቡድኑን በትኖ ከወር በላይ ከውድድር ርቆ የቆየ ሲሆን ወደ ልምምድ ሲመለስም ሶስቱ ተጨዋቾች ዳግመኛ ቡድኑን ሳይቀላቀሉ ቀርተዋል። ይህን ተከትሎም ክለቡ ተጨዋቾቹ የማይመለሱ ከሆነ የቅጣት እርምጃ እንደሚወስድ መግለፁን መዘገባችን ይታወሳል።
በዚህም መሰረት ወልዲያ ዛሬ ሶስቱ ተጨዋቾች ላይ የሁለት አመት እገዳ የጣለ ሲሆን እያንዳንዳቸውም አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር እንዲከፍሉ ወስኗል።
በተያያዘ ዜናም ወልዲያ ከወላይታ ድቻ ጋር የሚያደርገው የፕሪምየር ሊጉ ተስተካካይ ጨዋታ ከነገ ወደ እሁድ እንደተላለፈ ሰምተናል።