ወልዲያ ከነማ ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላቀለ

ዛሬ 8 ሰአት በተደረገው የብሄራዊ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ወልዲያ ከነማ ወልቂጤ ከነማን 3-1 በማሸነፍ የ2007 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ተቀላቅሏል፡፡

ወልቂጤ ከነማዎች በመጀመርያው አጋማሽ በሳዲቅ ሴቾ አማካኝነት ባስቆጠሩት ግብ እስከ 78ኛው ደቂቃ ድረስ 1-0 መምራት ቢችሉም በ6 ደቂቃዎች ውስጥ በተስፋዬ ነጋሽ (2) እና በተስፋሚካኤል በዛብህ (የፍፁም ቅጣት ምት) ባስቆጠሯቸው 3 ግቦች የጨዋታውን መንፈስ በቅፅበት ቀይረውታል፡፡

ወልዲያ ከነማ ረቡእ ሐምሌ 16 ቀን 2006 ከአዳማ ከነማ ጋር የፍፃሜውን ጨዋታ ሲያደርግ ሱሉልታ ከነማ እና ወልቂጤ ከነማ ደረጃ ጨዋታቸውን ያካሄዳሉ፡፡

ወልዲያ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማለፉን ተከትሎ የሀገሪቱ ትልቁ ሊግ 42ኛውን ክለብ በ2007 ይቀበላል፡፡

ያጋሩ