ከ17 አመት በታች ቡድኑ በሜዳው አቻ ተለያየ

በ2015 በኒጀር ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ17 አመት በታች ቻምፒዮን-ሺ ለማለፍ ዛሬ ከጋቦን አቻው ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን 0-0 አቻ ተለያይቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በፓስፖርት እና የምዝገባ ችግር ምክንያት 7 ተጫዋቾቹን ሳይዝ ጨዋታውን የጀመረ ሲሆን በተጠባባቂ ወንበር ላይ የነበረው ተጫዋችም አንድ ብቻ ነበር፡፡

በጨዋታው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች መልካም አቋም ያሳዩ ሲሆን ተጫዋቾቹ በተናጠል ያሳዩት አቋም በርካቶችን አስደስቷል፡፡

በሌሎች ከ17 አመት በታች ቻምፒዮን-ሺፕ ማጣርያዎች የተመዘገቡት ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

ዛምቢያ 1-0 ቦትስዋና

ሞዛምቢክ 2-1 አንጎላ

ዩጋንዳ 4-0 ሩዋንዳ

ካሜሩን 2-0 ቡርኪናፋሶ

ቤኒን 1-0 ማሊ

ታንዛንያ 0-0 ደቡብ አፍሪካ

ያጋሩ