ኢቢሲ የተመረጡ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ሊያስተላልፍ ነው

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን እና ኢቢሲ የተመረጡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን እና የብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎችን ለማስተላለፍ የሚያስችል ስምምነት በኢቢሲ የስብሰባ አዳራሽ ተፈራርመዋል፡፡ ጨዋታዎቹ በኢቢሲ 3 ላይ የሚተላለፉ ሲሆን የ2008 የውድድር ዓመት መክፈቻ ጨዋታ በልዩ መልኩ ለማስተላለፍ እንደታሰበ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡
በ1990 እንደገና የተቋቋመው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እስካሁን ድረስ የቴሌቪዥን ስርጭት አልነበረውም፡፡ በተለያዩ ግዜያት ግን ውድድሮች ቀጥታ ስርጭት አግኝተዋል፡፡ ለአብነት ያክል በ2003 ዓ.ም. የውድድር ዘመን የተወሰኑ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች የቴሌቪዥን ስርጭት አግኝተዋል፡፡ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ እግርኳስ መልካም ሲሆን ፌድሬሽኑ በስምምነቱ ላይ ከክለቦች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ጨምሮ ገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *