ሀዋሳ ከተማ ከሁለት ተጫዋቾቹ ጋር ተለያይቷል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሊጉ ወጣ ገባ አቋም እያሳየ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ በፈለግኩት ልክ አላገኘዋቸውም ካላቸው ሁለት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

ከክለቡ የተስፋ ቡድን በ2007 ወደ ዋናው ቡድን ያደገው ፍርዳወቅ ሲሳይ በ2008 የውድድር ዘመን ፕሪምየር ሊጉ ላይ 8 ግቦችን አስቆጥሮ የበርካቶች አይን ውስጥ ቢገባም ያለፉትን ሁለት አመታት ግን የታሰበውን ያህል እድገት ባለማሳየቱ እና በዚህ አመትም በቂ የመጫወት እድል ባለማግኘቱ በክለቡ ቀሪ የስድስት ወራት ኮንትራት እያለው በስምምነት ተለያይቷል፡፡

ሌላኛው ከክለቡ የተለያየው ሳዲቅ ሴቾ ነው። ሳዲቅ ሴቾ በክረምቱ ሀዋሳን ከተቀላቀሉ አዳዲስ ተጫዋቾች መካከል ቢሆንም በጉዳት ምክንያት በአንድም የሊጉ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ መጫወት አልቻለም። የቀድሞው የሼር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያ ቡና አጥቂ የ18 ወራት ኮንትራት ቢኖረውም ከክለቡ ጋር ባደረገው ስምምነት ምክንያት ከክለቡ ጋር ተለያይቷል፡፡

ሀዋሳ ከተማ በዝውውር መስኮቱ አብዱልከሪም ሀሰን እና አላዛር ፋሲካን ማስፈረሙ የሚታወስ ሲሆን ባለፉት ሶስት አመታት ከተስፋ ቡድን አድገው በሜዳ ላይ ድንቅ እንቅስቃሴን እያደረጉ የሚገኙ ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ድርድር ላይ እንደሆነም ሰምተናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *