ባሪ ለዱም ለሲዳማ ቡና ፈረመ

ሲዳማ ቡና ናይጄሪያዊውን የጅማ አባ ቡና አጥቂ ባሪ ለዱምን ባልተገለፀ ዋጋ አስፈርሟል፡፡ እየተካሄደ ባለው የብሄራዊ ሊግ ማጠቃለያ ጨዋታ ላይ 3 ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ባሪ የሁለት ዓመት ውል ከሲዳማ ጋር ተፈራርሟል፡፡ በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ያለው ሲዳማ ባሪ አምስተኛው ፈራሚ ሆኗል፡፡
ከዝውውሩ በኋላ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየቱን የሰጠው ባሪ ደስተኛ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

 

“በጣም ጓጉቻለው፡፡ ለኔ አዲስ ለውጥ ነው፡፡ ከብሄራዊ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ የተደረገ ሽግግር፡፡ ለሲዳማ በመፈረሜ ደስተኛ ነኝ፡፡
ሲዳማ ቡና ከኤሌክትሪክ ጋር የተለያየውን ሃይቲያዊ አማካይ ሳውረን ኦላሪስን አስፈርሟል፡፡”

 

በክረምቱ የዝውውር መስኮት አንተነህ ተስፋዬን እና ሙሉአለም መስፍንን ከአርባምንጭ ከነማ፣ ሚካኤል ለማን ከደቡብ ፓሊስ እና ዘላለም ታደለን ከወላይታ ድቻ ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡ ባሪ ከሳውረን በመቀጠል የፈረመ ሁለተኛው የውጭ ሃገር ዜጋ ነው፡፡

ያጋሩ