ፊፋ በየሁለት ወር በሚያወጣው የሴቶች እግርኳስ ሃገራት ደረጃ ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በያዝነው ወር ደረጃ ውስጥ ሳይካተት ቀርቷል፡፡
ሉሲዎቹ ባለፉት 18 ወራት ምንም ጨዋታ አለማድረጋቸው ከደረጃው እንዲወጡ አድርጓቸዋል፡፡ ፊፋ በደረጃው ላይ የሚያካትታቸው ሃገራት በ18 ወራት ውስጥ ጨዋታዎችን ያደረጉ ሃገራትን ቡድኖችን ብቻ ያካተት ሲሆን ኢትዮጵያ ከሴካፋ ሴቶች ቻምፒየንሺፕ የደረጃ ጨዋታ ዩጋንዳን 4-1 ካሸነፈች በኃላ ከጨዋታ ርቃለች፡፡ የማጣሪያ ጨዋታዎች ብቻ ሲኖሩ ጨዋታውን የሚያደርገው ቡሄራዊ ቡድኑ ባለፈው አመት ላይ እንደወንድ ብሄራዊ ቡድኑ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሲያደርግ አይታይም፡፡
ልክእንደኢትዮጵያ ሁሉ ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ሜቅዶንያ፣ ኤል ሳልቫዶር እና ኒካራጉዋ በደረጃውን ላይ ለ18 ወራት አንድም ጨዋታ ባለማድረጋቸው ከደረጃው ውጪ ሆነዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ጋና ለምታስተናግደው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ሊቢያን ትገጥማለች፡፡ ሊቢያ በደረጃው ላይ ልክ እንደኢትዮጵያ አልተካተተችም፡፡