ኤልያስ ማሞ ለኢትዮጵያ ቡና ፈረመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ የጨዋታ አቀጣጣይ ኤልያስ ማሞ ለኢትዮጵያ ቡና መፈረሙን ክለቡ አስታውቋል፡፡

ክለቡ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፁ የኤልያስ ማሞን መፈረም ያስታወቀው እንዲህ ባለ ሁኔታ ነው፡

‹‹

በመሃል ሜዳ አጨዋወቱ የብዙዎችን ቀልብ የገዛው እንዲሁም ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እነ ዳዊት እስጢፋኖስን በያዘው ከክለቡ ኮከብ የመሃል ተጫዋቾች ጋር ጥምረት ሲፈጥሩ ለማየት የጓጉለት ኤልያስ ማሞ ለኢትዮጵያ ቡና ለሁለት አመት ለመጫወት ዛሬ ፊርማውን አኑሯል ፡፡

ኤልያስ ማሞ በቅድስ ጊዮርጊስ እና ንግድ ባንክ እንዲሁም በብሄራዊ ቡድኑ ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል ፡፡በአሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻ በሚመራው የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ለቀጣይ ሁለት አመታት በክለቡ የፊርማ ታሪክ ከፍተኛ በሆነ ብር ለመጫወት ዛሬ ሀምሌ 14/2006 . ፈርሟል ፡፡

››

ፎቶየኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የፌስቡክ ገፅ

ያጋሩ