በቅርቡ በብሩንዲ አዘጋጅነት ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ሴካፋ ዋንጫ የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን 23 ተጨዋቾችን በመምረጥ ሙሉ ዝግጅቱን ማድረግ ከጀመረ አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
ብሩንዲ አዘጋጅነት ለመጀመርያ ጊዜ የሚዘጋጀው ከ17 አመት በታች የሴካፋ ዋንጫ ፌዴሬሽኑ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና እና ረዳቶቹን ከሾመበት ማግስት ጀምሮ 120 ተጨዋቾችን በመጥራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ምልመላቸውን ካጠናቀቁ በኃላ ለውድድሩ የሚያስፈልጉትን 23 ተጨዋቾችን መርጦ በማጠናቀቅ ከባለፈው ከእሁድ ጀምሮ ቦሌ 24 ሜዳ አካባቢ በሚገኘው ብሉ ስካይ ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሜዳ ሙሉ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል ።
በዚህ የሴካፋ ዋንጫ ላይ ዘጠኝ ሀገሮች እንደሚሳተፉ የታወቀ ሲሆን ውድድሩ የፊታችን እሁድ መጋቢት 23 ይጀመራል ተብሎ በሴካፋ መገለፁን ተከትሎ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ነገ ወደ ቡጁንብራ ያቀናል ቢባልም ከሴካፋ በመጣው መልክት መሰረት በቅርቡ በሚገለፅ ቀን እስኪታወቅ ድረስ ዝግጅታቸውን እንዲቀጥሉ መነገሩን ሰምተናል ። ይህ መሆኑ ብሔራዊ ቡድኑ በቂ ሁኔታ ተጨማሪ የዝግጅት እንዲያገኙ ያስቻለ ቢሆንም በሌላ ወገን የውድድሩ መካሄድን በራሱ ስጋት ውስጥ ከቶታል።
ካፍ በአዲሱ አሰራሩ በ2019 በታንዛንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ በየዞኑ ሀገራት በሚያስመዘግቡት ውጤት በኮታ እንዲያልፉ የሚደረግ ሲሆን በዚህም መሰረት በሴካፋ ውድድር ውጤት የሚያስመዘግቡ ቡድኖች ወደ አፍሪካ ዋንጫው የሚያመሩ ይሆናል።
ለሴካፋው ውድድር የተመረጡት የመጨረሻዎቹ 23 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው:-
ግብ ጠባቂዎች (3)
ምንተስኖት ጊምቦ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ተስፋሁን አዲሴ (አዳማ ከተማ)፣ ስጦታው አበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ተከላካዮች (7)
ታሪኩ ይርጋ (ኤሌክትሪክ)፣ አዛርያስ አቤል (ወላይታ ድቻ)፣ ሙአዝ ሙህዲን (አዳማ ከተማ)፣ ፀጋአብ ዮሀንስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ አሸናፊ ጌታቸው (አካዳሚ)፣ ዳግም ወንድሙ (ሀዋሳ ከተማ)፣ በረከት ካሌብ (ሀዋሳ ከተማ)
አማካዮች (8)
ፀጋ ደርቤ (አካዳሚ)፣ ፍራኦል ደምሴ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሳሙኤል ጃጊሶ (ወላይታ ድቻ)፣ ሬድዋን ናስር (አአ ከተማ)፣ ሐጎስ ኃይሌ (መከላከያ)፣ ነብዩ ዳዊት (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሙሴ ከበደ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ኦባንግ ኦፓንግ (አካዳሚ)
አጥቂዎች (5)
አላሚን ከድር (አዳማ ከተማ)፣ ይበቃል ፈርጀ (አአ ከተማ)፣ አደም አባስ (አካዳሚ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሐብታሙ (ደደቢት)፣
ዋና አሰልጣኝ – ተመስገን ዳና
ረዳት አሰልጣኝ – ሙሉጌታ አይቼው
የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ – በለጠ ወዳጆ
የህክምና ባለሙያ – በቀለ ዘውዴ
የቴክኒክ ኃላፊ – ያሬድ አለማየሁ