ሳለዲን በርጊቾ ፣ ናትናኤል እና ራምኬል ከብሄራዊ ቡድኑ ተቀነሱ

ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በባህርዳር ዝግጅቱን እያደረገ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 3 ተጫዋቾች መቀነሳቸውን አስታውቋል፡፡

የተቀነሱት ተጫዋቾች ሳላዲን በርጊቾ ፣ ናትናኤል ዘለቀ እና ራምኬ ሎክ ሲሆኑ የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት አቶ ወንድምኩን አላዩ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ለስንብታቸው ምንያት የሆነው ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ልምምድ በመቅረታቸው ነው ብለዋል፡፡

‹‹ ሶስቱ ተጫዋቾች የግል ፍቃድ ጠይቀው ወደ አዲስ አበባ ሄደው ነበር፡፡ ነገር ግን እንዲመለሱ በተነገራቸው ቀን ባለመገኘታቸው የቡድኑ ልምምድ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድረዋል፡፡ በዚህም ራሳቸውን ከቡድኑ እንዳገለሉ ተቆጥሮ ከቡድኑ ተሰናብተዋል፡፡›› ብለዋል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው በተሸሙበት ወቅት የልምምድ ሰአት ለማያከብሩ ተጫዋቾች ቦታ እንደሌላቸው መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ከተቀነሱት ውስጥ ናትናኤል ዘለቀ ቡድኑን የተቀላቀለው በቅርቡ ሲሆን ራምኬል ሎክ ከኬንያ ጋር በተደረገው ጨዋ ቋሚ ተሰላፊ ነበር፡፡ ሳላዲን በርጊቾ ደግሞከቡድናችን ወሳኝ ተጫዋቾች አንዱ ናቸው፡፡

ያጋሩ