አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የመኪና አደጋ ደረሰባቸው

የሲዳማ ቡናው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ በግል መኪናቸው ሲጓዙ አደጋ እንዳጋጠማቸው ታውቋል፡፡ አሰልጣኙ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የብሄራዊ ሊግ ውድድር ተከታትለው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አሰበ ተፈሪ ላይ የመኪና አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

አሰልጣኙ የደረሰባቸው አደጋ ለክፉ የማይሰጥ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን በወገባቸው ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙት አሰልጣኝ ዘላለም በአሁኑ ወቅት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

የሲዳማ ቡናው አሰልጣኝ በብሄራዊ ሊጉን ተጫዋቾችን የመለመሉ ሲሆን የጅማ አባ ቡናው ባሪ ለዱምን ለማስፈረም መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

ያጋሩ