የ2018 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ ሲደረጉ ግብፅ ላይ ሊቢያ ኢትዮጵያን ታስተናግዳለች።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ወሩን በዝግጅት ያሳለፈ ሲሆን ያለፉትን ሁለት ሳምንታት በ25 ተጫዋቾች ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ እሁድ ምሽት ላይ 18 ተጫዋቾችን በመያዝ ጨዋታው ወደ ግብፅ አምርቷል። ትላንት ምሽትም ጨዋታው በሚደረግበት ፔትሮስፖርት ስታድየም የመጨረሻ ልምምድ ሰርቷል። የቡድኑ አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ቀለል ያለ ልምምድ ማድረጋቸውን እና ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በሊቢያ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት በጎረቤት ሀገር ግብፅ የሚደረገው ይህ ጨዋታ በካይሮ በሚገኘውና የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ኤንፒ በሚጠቀምበት ፔትሮስፖርት ስታድየም ላይ ይከናወናል። ጋናዊያኑ ቴሬሳ ብሬማንሱ በዋና ዳኝነት ፣ ቤትሪስ ታውድ እና ቴሬሳ አኮንግያም ደግሞ በረዳት ዳኝነት ጨዋታውን የሚመሩ ይሆናል።
በ2012 ኢኳቶሪያል ጊኒ ባስተናገደችው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ በ2014 በጋና ፣ በ2016 በአልጄርያ ተሸንፋ ወደ ውድድሩ ሳታልፍ መቅረቷ የሚታወስ ነው።
ሌሎች የዛሬ መርሀ ግብሮች
ረቡዕ መጋቢት 26 ቀን 2010
ኬንያ ከ ዩጋንዳ
ኮንጎ ሪፐብሊክ ከ ሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ
ታንዛንያ ከ ዛምቢያ
ሴኔጋል ከ አልጄርያ
ሀሙስ መጋቢት 27 ቀን 2010
ናሚቢያ ከ ዚምባብዌ
አርብ መጋቢት 28 ቀን 2010
ሞሮኮ ከ አይቮሪኮስት
ሌሶቶ ከ ስዋዚላንድ
ቅዳሜ መጋቢት 29 ቀን 2010
ቡርኪናፋሶ ከ ጋምቢያ