ሴካፋ U-17 | ወደ ቡሩንዲ የሚያቀኑ 20 ተጫዋቾች ታውቀዋል

ከሚያዚያ 6 – 20 በቡሩንዲ አዘጋጅነት በሚደረገው የሴካፋ ከ17 አመት በታች ዋንጫ በምድብ ሀ ከቡሩንዲ ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ጋር የተደለደለው የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ 23 ተጨዋቾችን በመያዝ ብሉ ስካይ ሆቴል ማረፊያውን አድርጎ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።

ሐሙስ ውድድሩ ወደሚካሄድበት ቡሩንዲ የሚያቀኑት ” ቀይ ቀበሮዎቹ ” አሰልጣኝ ተመስገን ይዟቸው የሚጓዛቸው 20 ተጫዋቾችን የለየ ሲሆን ሦስት ተጨዋቾችም ተቀንሰዋል። በረከት ካሌብ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ታሪኩ ይርጋ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ) እና ሐብታሙ (ደደቢት) ተቀናሾቹ ናቸው ።

አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በበቂ ሁኔታ ዝግጅታቸውን ማድረጋቸውን እና በተገኙ አጋጣሚዎች ከሁለት በላይ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ማድረጋቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል ።

ወደ ቡሩንዲ የሚያቀኑ የ20 ተጨዋቾቹ ስም ዝርዝር


ግብ ጠባቂዎች (3)

ምንተስኖት ጊምቦ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ተስፋሁን አዲሴ (አዳማ ከተማ)፣ ስጦታው አበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)


ተከላካዮች (6)

አዛርያስ አቤል (ወላይታ ድቻ)፣ ሳሙኤል ጃጊሶ (ወላይታ ድቻ)፣ ሙአዝ ሙህዲን (አዳማ ከተማ)፣ ፀጋአብ ዮሀንስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ አሸናፊ ጌታቸው (አካዳሚ)፣ ዳግም ወንድሙ (ሀዋሳ ከተማ)


አማካዮች (7)

ፀጋ ደርቤ (አካዳሚ)፣ ፍራኦል ደምሴ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሬድዋን ናስር (አአ ከተማ)፣ ሐጎስ ኃይሌ (መከላከያ)፣ ነብዩ ዳዊት (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሙሴ ከበደ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ኦባንግ ኦፓንግ (አካዳሚ)


አጥቂዎች (4)

አላሚን ከድር (አዳማ ከተማ)፣ ይበቃል ፈርጀ (አአ ከተማ)፣ አደም አባስ (አካዳሚ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)


የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ የምድብ ጨዋታውን ከሶማሊያ ጋር ሚያዝያ 6 የሚያደርግ ይሆናል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *