ሪፖርት | አዳማ ከተማ ወደ ድል በመመለስ ደረጃውን አሻሽሏል

ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሀ ግብር መካከል አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ አዳማ ከተማ ከ መከላከያ ያደረጉት ጨዋታ በአዳማ 1-0 አሸናፊነት ተገባዷል።

በአዳማ ከተማ በ17ኛው ሳምንት ደደቢትን ከገጠመው ስብስብ መካከል ከነዓን ማርክነህ እና ተስፋዬ በቀለን በደሳለኝ ደባሽ አና ኤፍሬም ዘካርያስ ምትክ በመጀመርያ አሰላለፍ ሲካተቱ በመከላካያ በኩል ቡናን ከገጠመወ ስብስብ ውስጥ በምንይሉ ወንድሙ ፣ ሽመልስ ተገኝ እና አቤል ማሞ ምትክ አብነት ይግለጡ ፣ የተሻ ግዛው እና ይድነቃቸው ኪዳኔን በማሰለፍ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት።
ፌዴራል ዳኛ ይርጋለም ወልደጊዮርጊስ በመሩት ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ እምብዛም ሙከራ ያልታየበት እና በመሀለ ሜዳ የተገደበ እንቅስቃሴ የተስተዋለበት ነበር። በ4ኛው ደቂቃ በግራ በኩል ከሱሌይማን መሐመድ የተሻገረለትን ኳስ ከነዓን ማርከነህ ተቆጣጥሮ ተከላካዮችን በማለፍ ወደ ግብ መትቶ ግብ ጠባቂው ያዳነበት የመጀመርያው ተጠቃሽ ሙከራ ሲሆን በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው በረከት ደስታ በ38ኛው ደቂቃ ከርቀት የመታው ኳስ ይድነቃቸው ኪዳኔ ሲመልስበት በ41ኛው ደቂቃ በጨዋታው ተገድቦ የዋለው ዳዋ ሆቴሳ ከቅጣት ምት በቀጥታ ሞክሮ አግዳሚውን ጨርፎ የወጣበት ኳስ በአዳማ በኩል በመጀመርያው አጋማሽ የተደረጉ ሙከረመዎቸች ናቸው።

እንግዶቹ መከላከያዎች በኳስ ቁጥጥር ረገድ የተሻሉ የነበሩ ቢሆንም በዚህ አጋማሽ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ ተስኗቸው ታይተዋል።

ከዕረፍት መልስ መከላከያዋች የመጀመሪያ 15 ደቂቃዎችን ተጭነው ተጫውተዋል። በተለይም በ51ኛው ደቂቃ ላይ ከርቀት ቴዎድሮስ ታፈሰ ወደ ግብ አክርሮ መትቶ ግብ ጠባቂው ጃኮ ፔንዜ ሲተፋው ተመስገን የሞከረው የሚጠቀስ ነበር። በ63ኛው ደቂቃ ተመስገን ገብረፃድቅ ወደ ግብ መትቶ ሙጅብ ቃሲም ተደርቦ ያወጣበትን ኳስ ያገኘው ከነዓን ወደፊት በማሻገር ለዳዋ ሲያቀበለው አዲሱ ተስፋዬ ደርሶ ቢያስጥለውም የተመቻቸ ቦታ ላይ የነበረው ቡልቻ ሸራ ወደግብ አክርሮ በመምታት ወደ ግብነት ለውጦ አዳማ ከተማን መሪ አድርጓል።

ከግቡ መቆጠር ባኋላ መከላካያዋች የአቻነት ጎል ለማስቆጠር ጥረት ያደረጉ ሲሆን ውዝግቦች ን ያስከተሉ ክስተቶችም ታይተዋል። በ64ኛው ደቂቃ ዳዊት እስጢፋኖስ ላይ ጥፋት ተሰርቷል በሚል የተሰጠው ቅጣት ትክክል አይደለም በሚል ምኞት ደበበ እና ተስፋዬ በቀለ ከዳኛው ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው ነበር። በዚሁ ክስተት በኋላም ጃኮ ፔንዜ ኳስ በቶሎ ባለማስጀመሩ የማስጠንቀቂያ ካርድ አይቶ ጨዋታው ተጀምሮ ኳስ ወደ መሀል ሜዳ በምታመራበት ወቅት የአርቢትሩ ፊሽካ ተሰምቶ በቀጥታ ለተስፋዬ በቀለ የቀይ ካርድ በማሳየት ከሜዳ እንዲሰናበት ወስነዋል። በውሳኔውም ከፍተኛ ተቃውሞ ከደጋፊው ሲሰማ ተስተውሏል።
ለተወሰነ ደቂቃ በውዝግብ የቆመው ጨዋታ ቀጥሎ መከላካያዋች በሳሙኤል ታዬ በ74ኛው ደቂቃ ፣ በዳዊት እስጢፋኖስ በ80ኛው እና አቅሌሲያስ ግርማ በ85ኛው ደቂቃ የግብ ሙከራ ቢያደርጉም ውጤቱን መለወጥ አልቻሉም። በተቃራኒው በ10 ተጫዋቾች ለመጫወት የተገደዱት አዳማ ከተማዎች መካላከልን ምርጫቸው አድርገው ውጤታቸውን አስጠብቀው በአሸናፊነት መውጠድ ችለዋል። በሜዳው ከተሸነፈ ሁለት አመት የሞላው አዳማ ከተማም ከ2004 በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ አበበ ቢቂላ ላይ መከላከያን መርታት ችሏል።

አስተያየቶች 


አሰልጣኝ ተገኔ አሰፋ – አዳማ ከተማ

ጨዋታው ጥሩ ነበር፤ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችለናል። ተጫዋች ባይወጣብን ኖሮ በሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ መንቀሳቀስ እንችል ነበር። ተጫዋቾች ትግዕስት ያስፋልጋቸዋል። በዚህ ላይ ወደፊት የምንሰራበት ይሆናል። ዛሬ ሳስት ነጥብ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት በሜዳችን መከላካያን ማሸነፍ ሳንችል የዘለቅንበትን ታሪክ ነው መቀየር የቻልነው።


አሰልጣኝ ስዩም ከበደ – መከላከያ

በ90 ደቂቃ ክፍተታችን በግልፅ ፊት መስመር ላይ ነበር። ይህ በሚቀጥለው ጨዋታ ይፈታል። ተጫዋቾቼን በቅጣት በማጣቴ የፊት መስመሩ ሳስቶ ነበር። በሚቀጥለው ጊዜ አዲሱ ፈራሚያችን ፍፁም ገብረማያምን የምንጨምር ስለሆነ ጥሩ እንሆናለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *