የፌዴሬሽኑ ፕሬዚደንት የግብፅን ጥያቄ እንዳልተቀበሉ አስታወቁ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁይነዲ በሻ ከግብፅ የመጣላቸውን የወዳጅነት ጨዋታ ግብዣ እንዳልተቀበሉ አስታውቀዋል፡፡ ግብፅ የአስዋን ግድብ ግንባታን መጠናቀቅ በማስመልከት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ለመጫወት ግብዣ ያረበች ሲሆን የግብፅ እግርኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ከኢትዮጵያ ጋር ለመጫወት መስማማታቸውን ተናግረው ነበር፡፡

አቶ ጁነይዲ ጨምረው እንደገለፁት ለኢትዮጵያ ከግብፅ በተጨማሪ ሌሎች ኃገራት ጥሪ ያደረጉ ሲሆን በ2 ቀናት ውስጥም ከየትኛው ብሄራዊ ቡድን ጋር እንደሚጫወቱ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ያጋሩ