ሆሳእና ከነማ ጅማን አሸንፎ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል

በ2፡00 በተደረገው ጨዋታ ሆሳእና ከነማ ጅማ ከነማን 3-1 አሸንፏል፡፡

ትላንት በተላለፈ ውሳኔ 4 ጨዋ እና 3 ሺህ ብር ተቀጥተው የነበሩት የጅማ ከነማው አሰልጣኝ ፋንታዬ አባተ የጨዋታ ቅጣቱ ተነስቶላቸው ቡድናቸውን ቢመሩም ከመሸነፍ አልዳኑም፡፡

ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት ጅማዎች ሲሆኑ አሸናፊ ይታየው በ17ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ መምራት ችለው ነበር፡፡ በ24ኛው ደቂቃ ሀብቶም ገ/እግዚአብሄር ግብ አስቆጥሮ ሆሳእና ከነማን አቻ አድርጓል፡፡ ከእረፍት መልስ በ62ኛው ደቂቃ የጨዋታው ኮከብ ዱላ ሙላቱ ሆሳእናን መሪ ሲያደርግ ጨዋታው ሊገባደድ ሽርፍራፊ ሴኮንዶች ሲቀሩ አምረላ ደልታ የሆሳእናን ድል አስተማማኝ አድርጎታል፡፡

image-96752b819738dd82148dad9245cca3336b6e81c35e2bb7efcd1114ffadf26846-V

ከጨዋታው በኋላ የሆሳእና ከነማው አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ በሰጡት አስተያየት ወደ ፕሪሚር ሊጉ ከመግባት የሚያግዳቸው ነገር እደሌለ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ጅማ ከነማን እንደምናሸንፍ አስቀድመን ተናግረን ነበር፡፡ ነገር ግን በሜዳ ላይ ፈትነውን ነበር፡፡ እኛም ያገኘናቸውን እድለች በአግባቡ አልተጠቀምንም፡፡ በማሸነፋችን ደስተኞች ነን፡፡››

‹‹ በግማሽ ፍፃሜው የምንገጥመውን ቡድን በሚገባ እናውቀዋልን፡፡ (ሀላባ ከነማ) ከዞናችን የመጣ ቡድን በመሆኑ አጨዋወታቸውን እናውቀዋለን፡፡ ወደ ፊት ከመጓዝ የሚያግደን ነገር የለም›› ብለዋል፡፡

የተሸናፊው ቡድን አሰልጣኝ ፋንታዬ አባተ በበኩላቸው በስነልቡናው ረገድ አለመዘጋጀታቸው ውጤት እናዳሳጣቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ከሼር ኢትዮጵያ ጋር በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ተረብሸናል፡፡ ያንን እያሰብን ወደ ሜዳ ስለገባን በስነልቡናው ረገድ የማሸነፍ ዝግጁነት አልነበረንም፡፡ በጨዋታው የበለጠው ቡድን አሸንፏል፡፡ ሆሳእናዎች እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ የድሬዳዋ ህዝብንም ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ ›› ብለዋል፡፡

ሆሳእና ከነማ በግማሽ ፍፃሜው ሃላባ ከነማን የሚገጥም ሲሆን ካሸነፈ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ፕሪሚየር ሊግ መግባቱን ያረጋግጣል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች እርስ በእርስ የሚጫወቱ በመሆናቸው አንድ የደቡብ ክለብ ፕሪሚየር ሊግ ከመግባቱ በተጨማሪ ከሁለቱ አንዳቸው በፕሪሚየር ሊጉ የተሳተፉ 43ኛው ክለብ ይሆናሉ፡፡

image-b9db13388f94fb763a611711bea89ab8f82495160abd034a51cf62c3a2759f89-V


 

ፎቶ – ከላይ የሆሳእና ተጫዋቾች ከድሉ በኋላ ፣ መካከል – የሆሳእናው አሰልጣኝ ግርማ ፤ ከታች የጨዋው ኮከብ ተብሎ በድሬዳዋ ስፖርት ኮሚሽን እና ወጣቶች ቢሮ በጋራ የተመረጠው ዱላ ሙላቴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *