ስብሰባው 08:08 ላይ ተጠናቋል። ክለቦች ውድድሩ በአስቸኳይ ከቆመበት እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
አቶ ጁነይዲ ባሻ
” በዚህ ሳምንት ከተለያዩ የመንግስት የፀጥታ መዋቅሮች ጋር ስብሰባ እናደርጋለን።
” የዳኞች ማህበር ከፌዴሬሽኑ ጋር ውይይት እና ድርድር ማድረግ አለበት።”
ትግል ግዛው (የዳኞች ማህበር)
” እኔ እየተናገርኩ ያለሁት በግሌ አይደለም። እውቅና እንዳለው ትልቅ ማህበር ነው። የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በሰጠኝ ስልጣን መሰረት ትላንት ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቻለሁ። ልጅህን ት/ቤት አትላክ ብትሉኝ ላልክ እችላለሁ። ዳኞችን ወደ ውድድር መልስ ብትሉኝ ግን ይህኝ የማድረግ ስልጣን የለኝም። ”
” የኢትዮጵያ ዳኞች ችግር እስኪፈታ ገንዘብ እየከሰርን መቀመጥ የለብንም። ካልሆነ ከጎረቤት ሀገራት ዳኛ አስመጥታችሁ ውድድሩ ይቀጥል። ” መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ (ቡና)
” ውሳኔያቸው ተቀባይነት ያለው እንዳለ ሆኖ ዳኞች የእግርኳሱ ባለድርሻ አካላት ናቸው። ፌዴሬሽኑም ዳኞችን እንደባለድርሻ አካልነታቸው አይቶ በአስቸኳይ ወደ ውድድር የምንመለስበት ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም። ” አቶ ሰለሞን በቀለ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
“እኛ በማንኛውም ጊዜ ከዳኞች ጋር ለመወያየት ዝግጁ ነን። በፍጥነት እልባት ልናበጅለት ይገባል። ” አቶ ጁነይዲ ባሻ
ከይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ
” ከዲሲፕሊን ኮሚቴ የቀረበው ነገር ‘ ይሉሽን ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ አይነት ነው። ‘ ሌላውን ትተን የወልዲያን ውሳኔን በተመለከተ የወሰንነው ውሳኔ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን። በወልዲያ ላይ ከ7 ነጥቦች መካከል ሁለት ብቻ ነው ያሻሻልነው። ”
ከዲሲፕሊን ኮሚቴ
” ከዚህ በፊትም ዳኞች ሲደበደቡ ክለቦችን እና ደብዳቢዎችን ቀጥተናል። ነገር ግን ቅጣቶቹ ሲሻሩ ነው የተመለከትነው። ”
” ክለቦችን ማውረድ ቀላል ነው ህጉም ይፈቅዳል። ነገር ግን ወንጂ ከወረደ በኋላ አሁን የት ነው ያለው? ”
” የምናቀርበው የመፍትሄ ሀሳብ በክልል ፖሊስ ፊት ውድድር ማድረግ መቆም አለበት። ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመነጋገር ውድድሮች መደረግ አለባቸው። ”
” አንቀፅ 72 ላይ ሜዳ ሲወረር እና ከዛ በላይ ላሉ ድርጊቶች የሚያስቀጣው ቅጣት በግልፅ አማርኛ ተቀምጧል። በዛ ነው ወልዲያ ላይ ቅጣት ያስተላለፈው። ”
” ወልዲያ ላይ የተላለፈው ቅጣት የታጠፈበት ምክንያት መመርመር አለበት። ጥፋቱ የማን እንደሆነ ተጣርቶ መጠየቅ አለብን። ግልፅ የሆነን ድርጊት ከአንድ አመት ቅጣት በአንድ ጊዜ ወደ ሶስት ጨዋታ ማውረድ ተቀባይነት የሌለው ነው። ”
” እኛ አማራ እና ትግራይ ክለቦች በሜዳቸው እርስ በእርስ እንዳይጫቱ አልወሰንንም። ውሳኔው የሊግ ኮሚቴው ሊሆን ይችላል። ”
” ችግሮች እንዳሉ ሆኖ የፍትህ አካላት ዋንኛ የችግሩ አካል ናቸው መባሉን እንቀበላለን። በፀደቀ የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ቅጣቶችን ያስተላልፋል። ሆኖም ችግሩ የተባባሰው ስራ አስፈፃሚው እና ይኝባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሲቀለብሱ ስለሚታይ ነው። እኛም ጭምር የምንቀጣው ቅጣት ማነስ ይታይበታል። እኛ ቅጣት የምናስተላልፈውን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በምህረት ውሳኔዎችን የሚቀለብስበት መንገድ አግባብ አይደለም።
” ዛሬ ልንፈታተሽ ይገባል። የዲሲፕሊን ኮሚቴ የሚወስነውን ውሳኔ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ይሽረዋል። በዚህም ምክንያት ያለ አግባብ የተለያየ ስም እንዲሰጠን እየተደረገ ነው።”
” ቅድሚያ የፍትህ አካል ሲዋቀር ባለሙያ ሰዎች ናቸው ወይ የመጡት? ከህግ እውቀት በተጨማሪ የስፖርት እውቀት አለው ወይ? ታማኝነታቸው ታይቶ ነው ወይ የተዋቀረው? ችግር ሲፈጠርስ አዋቃሪው አካል ከስር ከስር ችግርሮችን ለመቅረፍ ጥሯል ወይ? የሚሉ መታየት ነበረባቸው። ”
” ሊመረጥ የሚገባው እና ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔ መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱም የሚመርጠኝ አካል በኔ እምነት ሊያጣ አይገባም። ”
ከሲዳማ ቡና
” የዲሲፕሊን ኮሚቴ ቅጣቶች ክለቦችን እንዲጠነቀቁ የሚያደርጉ አይደሉም። የላሉ እና ወዲያው የሚነሱ ቅጣቶች ነው ያሉት። ”
” መንግስት ህዝቡን ለማስተዳደር የሚያወጣቸው ህጎች ስታድየም አካባቢ የማይተገበሩት ለምንድነው? አሁን ያለው እውነተኛ እግርኳስ አይደለም.. ክለቦች እያገኙ ያሉትም እውነተኛ ውጤት አይደለም። ”
” የዳኞች ውሳኔ ትክክል ነው። እንኳን ዳኞች ክለቦች ራሱ ተጓጉዞ የመጫወት ዋስትና ስለሌለን ማቋረጥ አለብን ማለን እንችላለን። ”
ከዳኞች ማህበር
” ትንሽ ነገር ተጋነነ መባሉ አግባብነት የለውም። ዳኛ እየተሳደደ ሲደበደብ ትልቅ ጉዳይ ካልሆነ ሰው ሲሞት ነው ወይ ትልቅ ጉዳይ የሚሆነው። ጥይት እና ጭስ መተኮስ እኮ ያለበት ጠላትን ለማባረር እንጂ ስታዲየሞች ላይ አይደለም። ”
” ወንጂ ከዚህ ቀደም ባጠፋው ጥፋት እኮ ከፕሪምየር ሊጉ ነው እንዲወርድ የተደረገው። ፌዴሬሽኑ አሁን እንዲህ አይነት ውሳኔ ለመወሰን ለምን ወኔ አጣ? ”
” ክለቦች ችግሩን ያወገዛችሁበትን ንግግሮች እናደንቃለን። ከዚህ ባለፈ በዳኞች ላይ የሚሰሙ ሀሜቶችን ያለ ማስረጃ ማቅረብ የለብንም። ”
” ማህበራችን ያሳለፈው ውሳኔ የዘገየ ቢሆንም ተገቢ ነው ብለን እናምናለን። ”
” ጥፋት አጥፍተው የሚቀጡ ግለሰቦች በሚድያ ቀርበው ሲያወያዩ እናያለን። ችግር የደረሰባቸው ዳኞች ግን የሚድያ ሽፋን ሲያገኝ አናስተውልም። ”
ከወላይታ ድቻ
” በእግርኳስ ላይ የታየው የዘረኝነት እና ሌሎች ችግሮች የሚቀረፉት ኳሱ ላይ ስንሰራ ነው። ድቻ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ያደረገው ጉዞ መላው ሀገሪቱን እንዴት አንድ ማድረግ እንደቻለ አይተናል።”
“የእግርኳስ ህጎች እና ደንቦችን ለደጋፊዎቻችን ግንዛቤ ማስጨበጥ ይኖርብናል። በአእምሮ ላይ የሚሰራ ስራ ሊቀድም ይገባል። ”
” እግርኳሱ አድጓል ሲባል እየሰማሁ ነው። ከየትኛው ሀገር ጋር ተወዳድረን ነው አደግን የተባለው? ”
ከጅማ አባጅፋር
” ህግ በአግባብ የማይተረጎም ከሆነ የዲሲፕሊን እና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ መኖር የለባቸውም። የሚያጠፉት ግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ ተለይተው መቀጣት አለባቸው። ”
” ውሳኔ አንቀፅ ተጠቅሶ የሚተላለፍ ከሆነ ለምን በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ እንዲሁ በደፈናው ቅጣት ይነሳል? ”
” የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ጉዳይ የሁላችንም ሊሆን ይገባል። ከክለብ አቅም በላይ ከሆነ ደግሞ ሌሎች መፍትሄዎች ሊተገበሩ ይገባል እንጂ ያለሜዳቸው እንዲጫወቱ መደረግ የለበትም። እግርኳስ ሊያቀራርብ ሲገባ የችግር ማባባሻ ሊሆን አይገባም።”
” የዳኞች ማህበር ውሳኔ አስደንጋጭ ነው። ውሳኔው እየፈሰሰ ያለውን የሀገር ሀብት ያማከለ መሆን አለበት። እንዳውም በተቋረጠው አንድ ሳምንት ውስጥ ፌዴሬሽኑ ዳኞችን አናግሮ ወደ ውድድር መመለስ አለብን። ”
ከፋሲል ከተማ
” የዳኞች ማህበር የወሰነውን ውሳኔ እንደ ክለብ አንደግፈውም። ጥያቄያቸውን እንዲመለስ እየተጠየቁ ውድድሩ መቀጠል አለበት ብለን እናምናለን። ”
” የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር የሌለበት ክለብ የለም። ነገር ግን ችግሩ በክለብ ብቻ ይፈታል ማለት አይቻልም። ”
” ሚድያዎች ሲፈለግ የሚያንቆለጳጰሱበት ሲፈለግ የሚዘልፉበት ተቋም መሆን የለባቸውም። በታማኝነት መስራት አለባቸው። ”
” ውሳኔዎች ላይ የትኛውም አካል ደስተኛ አይደለም። ይህ መታየት አለበት። ”
” የአማራ እና ትግራይ ክለቦች እርስ በእርስ በየሜዳቸው እንዳይጫወቱ የተወሰነበት ምክንያት ግልፅ አይደለም። በችግሮች ላይ እርምጃ እንደመውሰድ ክልል ከክልል ህዝብ ከህዝብ እንዳይገናኝ መደረጉ አግባብ አይደለም። ”
ከወልዋሎ
” አሁን ስለተከሰተ ጉዳይ ብቻ ማንሳት አግባብ አይደለም። ወልዋሎ በብርሀን ፍጥነት ለወሰደው እርምጃ ሊደነቅ ይገባዋል። ሌሎች ላይ ጣት ከመቀሰር በፊት ክለቦች ራሳችንን መፈተሽ አለብን። አሁን እዚህ ላይ ስለ ወልዋሎ ብቻ ማውራት ለችግሩ መፍትሄ አይሆንም። ”
” ስፖርታዊ ጨዋነት የሚሰፍነው ክለቦች ከክለቦች ሲቀራረቡ ነው። ለዚህ ደግሞ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ መሆናችን ሲነገር አንሰማም። ችግሩ ብቻ ነው ተጋኖ እየተወራ የሚገኘው። ”
ከቅዱስ ጊዮርጊስ
” አሁን እየታዩ ያሉት የብሔርተኝነት ፣ የዘረኝነት ጉዳዮች ከፌዴሬሽኑ እና የክለቦች አደራጀት ችግር የመጣ ነው። ”
” የተቋረጠው ጨዋታ አዲስ ነገር ነው ወይ? ከዚህ የባሰ ችግር አልነበረም ወይ? ሲጠራቀም የመጣ ችግር በመሆኑ በቀላሉ የሚፈታ ችግር አይደለም። በጊዜው ሳይቃጠል በቅጠል መሆን አለበት ብንልም ሚገሳናገኝ ቆይተናል።”
” የፌዴሬሽኑ ደንቦች ከፍተኛ የህግ ክፍተት አለባቸው። ወደ ዳኞች እና ኮሚሽነሮች ጥራት መምጣት አለብን.. ክለቦችን በእኩል አይን ማየት አልተቻለም.. ሊጉን እየመራው ያለው ማን እንደሆነ አይታወቅም.. ውድድሮች ከተቋረጡ አጠቃላይ የእግርኳስ ውድቀት ነው። ”
” የዳኞች ማህበር እስከ ግንቦት 20 ያቋረጠበት ምክንያት አልገባኝም። ቀኑን የመረጠው ከማን ነፃ ለመውጣት አስቦ ነው? ”
” ጨዋታው እግርኳስ መሆኑ እየተረሳ ነው። ”
” ውድድሩ ዘንድሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ መጣር አለብን።”
” በዳኞች ላይ ለደረሰው ጉዳት በክለባችን ስም ይቅርታ እንጠይቃለን። ችግራችሁ ችግራችን ነው። ”
ከወልዋሎ
” የዳኞችን ውሳኔ ብናከብርም ውድድሮች መቋረጥ የለባቸውም። ፌዴሬሽኑ ኃላፊነት ወስዶ በማግባባት በቶሎ ወደ ውድድር መግባት አለብን። ዳኞችም ያለውን ሁኔታ ተመልክተው ውሳኔያቸውን ያጤናሉ ብለን እናምናለን። ”
” ሁላችንም ከስሜት በፀዳ መልኩ ከጊዜያዊ ጉዳይ መዝለልና ዘላቂ ለውጥ ማምጣት አለብን። ሚድያም ሚዛናዊ ሊሆን ይገባል። ”
” እያጋጠመ ያለውን ፈተና በትክክል ካላየነው ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማግኘት እንችላለን የሚል እምነት የለኝም። ”
” እግርኳሱ እንደደረሰበት ደረጃ አመራሩ ያለበት ደረጃ ዝቅተኛ ነው። በዚህ ጉዳይ ፍኖተ ካርታ መዘጋጀት አለበት። ይህን ለሚሰሩ ግለሰቦችም ኃላፊነት መስጠት አለብን።”
” ሁሉንም ነገር ለፌዴሬሽን መተው የለብንም። ሚድያው ፣ ክለቦች ፣ የክልል ፌዴሬሽኖች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የየድርሻቸውን መወጣት አለባቸው። ”
አቶ ጣሃ (ሀዋሳ)
” ሚድያው ለእግርኳሱ አሁን ያለበት ሁኔታ ችግር እየፈጠሩ የሚገኙ ናቸው። ”
” ከፀጥታ አካላት ጋር ተባብረን እንሰራለን ሲባል እንሰማለን። ነገር ግን እየተሰራ ያለ ስራ የለም። ”
” የዳኞች እና ኮሚሽነሮች ሪፖርት ችግር አለበት። የተፈፀሙ ነገሮች እየተድበሰበሱ ይቀራሉ። ”
” የፌዴሬሽኑ ስራዎች ተደራርበው መሰራት የለባቸውም። ስራን በትክክል ለመስራት ተደራራቢ ኃላፊነቶች መቃለል አለባቸው።”
ከመከላከያ
” መከላከያ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ድርጊቱን ያወግዛል። ዳኞች እንደ ግለሰብ ማህበሩ እንደማህበር ሊከበሩ ይገባል። ፊሽካ በተነፋ ቁጥር የሚደርሱ ወከባዎች ለእግርኳሱ አደገኛ ሆነው አግኝተናቸዋል። ለነዚህ ጉዳዮች እያንዳንዱ ክለብ ተጠያቂ ናቸው። ጨዋታዎች ከመጀመርራቸው በፊት ሊደረጉ የሚገባቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች ሊደረጉ ይገባል።”
ከመቐለ ከተማ
” ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት ስናስብ ለዚህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ አካላትን በስም በቁጥር እየገለፅን እውነታውን ካልተናገርን ችግሩን በደፈናው ብቻ መግለፅ መፍትሄ ያመጣል ብዬ አላምንም።”
” የመጀመርያው በደጋፊዎች መካከል ያለው የስፖርታዊ ጨዋነት ተግዳሮች ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር አለ ወይ? ደጋፊዎች ሲጣሉ እንጂ ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት ሲነገር መቼ ሰምተን እናውቃለን። ኃይማኖት እና ዘር ተለይቶ ሲሰደብ እንደ ምርቃት የሚቆጥር አመራር ካለ ችግሩ ሊቀረፍ አይችልም። ”
“እየታየ ያለው ዘረኝነት እግርኳስን ብቻ ሳይሆን ሀገርን ነው የሚያጠፋው። የምስራቅ አውሮፓ እግርኳስ በዘረኝነት እንዴት እንደወደቀ ትምህርት መውሰድ እንችላለን። አአ ላይ ላይሰማ ይችል ይሆናል እንጂ በየክልሉ የማይነሳ ዘር የለም።”
” እኛም በበኩላችን ዳኛን የሚያዋክብ እና ልብስ የሚጎትትን ተጫዋች የምንቀጣበት ደንብ አለ። ”
” እግርኳሱ አድጓል። ነገር ግን እድገቱን የሚመጥን አመራር የለም። ”
ከአዳማ ከተማ
” የዳኞች ማህበር ውሳኔን እንቀበላለን። ይህ ችግር በየጊዜው ስንመለከት የቆየነው እና መፍትሄ ሳይበጅለት ቀርቶ እዚህ የደረሰ ነው። ”
” የሚወሰኑ ውሳኔዎች ወዲያው የሚሻሩበት መንገድ ለዚህ ችግር መባባስ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የአማራ እና ትግራይ ክለቦች በየሜዳቸው እርስ በእርስ ጨዋታ የማያደርጉበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው። ሀገሪቱ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ስለተገኘች ውድድሮች በአግባቡ መከናወን አለባቸው። እንደ አዳማ የዳኞችን ውሳኔ ብናከብርም ውድድሮች ከሰኔ 30 በፊት የሚጠናቀቁበት መንገድ ሊኖር ይገባል።”
ከደደቢት
” ውድድሩ መቋረጡ አደጋ አለው። ከፋይናንስ እና አየር ንብረት ጋር በተገናኘ ሊታሰብበት ይገባል።”
” ክልል ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል። ዳኞቹ እየፈሩ ማጫወት የለባቸውም። ከዚህ በተጨማሪ የመናበብ ችግር አለባቸው። አንዱ ያፀደቀውን ሌላኛው ይሸረዋል።”
“አሁን ያለንበት ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ነው። በዚህ ወቅት አድማ መምታች ይቻላል ወይ የሚለው መታየት አለበት። በአድማ ምክንያት በሚቋረጠበት ወቅት ወጪያችንን የሚሸፍነው ማነው? ከሰኔ 30 በኋላ ምን ሊደረግ ነው? አነዚህ መታሰብ አለባቸው። ይህን ስል የዳኞች መብት አይከበር ማለቴ አይደለም። መብታቸው በህግ ሊከበር ይገባል። ዳኛ ተማቶ እጁን በኪሱ ከቶ ሲንጎማለል የነበረው የወልዋሎ የቡድን መሪ እኮ በአሁኑ ሰዓት እስር ቤት መሆን ነበረበት። ፍትህ ለአንዱ ተከብሮ ለሌኛው የሚነፈግበት ሀገር መሆን የለበትም። ደብዳቢው በኩራት እጁን ኪሱ ውስጥ ከቶ ሲሄድ ሌላኛው ተደብድቦ ፍትህ ማጣት የለበትም። ”
“የጨዋታዎችን መቋረጥ እንደ ኢትዮጵያ ቡና አንቀበለውም። የምናወጣው በርካታ ወጪ መታሰብ ነበረበት።”
“በመከላከያ እና ወልዋሎ ጨዋታ ላይ ዳኛው የተደበደበበትን ድርጊት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ ፣ ተጫዋቾቻችን እና ደጋፊዎቻችንን አሳዝኗል። የሀዘን መግለጫ ለማን እንደምንልክ ራሱ አናውቅም። ይህ ሁኔታ እዚህ እንዲደርስ ያደረጉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው የሚለውን ማየት አለብን። የእኛን ታሪክ ላንሳ፡- በ2008 ጎንደር ላይ ከዳሽን ቢራ ጋር ስንጫወት ወዛደሮቹን አውጥቶ አስደብድቦናል። በግለሰቦች ላይ እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ ጉዳት ደርሷል። ያን ችግር የሚያሳይ ቪድዮ ጭምር አቅርበን ለፌዴሬሽኑ ብናሳውቅም የተወሰነ ነገር የለም። ከዛም በመቀጠል በተለያዩ ቦታዎች የህይወት እና የአካል መጉደል ሲደርስ ምንም የመፍትሄ እርምጃ ሳይወሰድ እዚህ ደርሰናል። ”
“እግርኳስ የሰላም መድረክ ነው። ይህን ስብሰባ የጠራንበት ምክንያትም የስፖርታዊ ጨዋነቱ ላይ እየተከሰቱ ባሉ ችግሮች ላይ ለመምከር ነው።” አቶ ጁነይዲ ባሻ
03:30 ስብሰባው በአቶ ጁይነዲ ባሻ የመክፈቻ ንግግር ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የፕሪምየር ሊግ ክለቦች የምክክር መድረክ