የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ

7:32 – አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔው የምርጫ ኮድ በማፅደቅ ፣ የአስመራጭ ኮሚቴ እና ቅሬታ ሰሚ አባላትን በመምረጥ ተጠናቋል።


7፡29 – ” ለሃገራችን ሰላም ማድረግ አለብን፡፡ ምርጫውን ጁን 3 ብለናል ፤ ስለዚህም ከዚህ በኃላ አይራዘምም፡፡ በዳኞች በኩል በተመለከተ በአንድ በኩል ክለብ መስርቱ እያልን ይሄ መፈጠሩ ትክክል አይደለም፡፡ በሌላው ጎን ደግሞ ዳኞቻችን ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የኛው አካል ናቸው፡፡ አንደኛው እጄ ሌላኛውን እጄ መምታት የለበትም፡፡ እናሳክማለን፣ ኢንሹራንስም እንገባለን ብለናል፡፡ እግርኳሱ መጠቀል አለበት፡፡ ዳኞቻችን የደረሰባቸውን ችግር እንፈታለን፡፡ ” ፕሬዝደንት ጁነይዲ


7፡27 – ” አንድ ነገር መናገር እፈልጋለው፡፡ እየተፈጠሩ ያሉ ነገሮች አይተናል በተለይ አሁን በቅርቡ በተፈጠሩ ጉዳይ ላይ ሰው በሚዲያም ሰው እየሰማ ነው፡፡ የዳኞችን ኮሚቴ ሆደ ሰፊ ሆኖ እግርኳሱ መጀመር አለበት፡፡ “የቀድሞ ፕሬዝደንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ


7:25 ተመራጭ ግለሰቦች በቀድሞው ፕሬዝዳንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ አማካኝነት ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።


7፡19 – ሶስቱ የይግባኝ ኮሚቴ አባላት ሆነው የተመረጡት


አቶ ሽፈራው አመኑ (ሰብሳቢ)

አቶ ኦባንግ ሀላባ

አቶ ገዛኸኝ ለማ

ቀሪዎቹ ተጠባባቂ ሆነዋል፡፡


7፡18 – የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ እጩዎች እና የተሰጣቸው ድምፅ

አቶ ገዛኸኝ ለማ – 79

አቶ ሽፈራው አመኑ – 106

ወ/ሮ ማህተ አምባዬ – 70

አቶ ኦባንግ ሀባላ – 86

አቶ ኤፍሬም ሣህሌ – 46


7፡05 – ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ዕጩ ሆነው የቀረቡ

ገዛኸኝ ለማ (ማስተርስ በእግርኳስ ዲፕሎማ በስፖርት ሳይንስ እና በህግ ድግሪ ያላቸው የቀድሞ ተጫዋች እና የአዳማ ከተማ መስራች)

ሽፈራው አመኑ (በህግ ዲግሪ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እ ፌደራል ፖሊስ ጠበቃ)

ማህተ አምባዬ (በኢኮኖሚክስ ዲግሪ የወጋገን ባንክ የቦርድ አባል የነበሩ)

አቦንግ ሀባላ (በህግ ዲፕሎማ እና በማኔጅመን ዲግሪ በጋምቤላ ክልል መንግስት በተለያዩ ሃላፊነቶ ያገለገሉ)

አቶ ኤፍሬን ሣህሌ (ማስተርስ በልዩ ፍላጎት ትምህርት እና ዲግሬ በሳይኮሎጂ በመምህርነት ሙያ ላይ የሚገኙ)

እጩዎቹ ራሳቸው እያስተዋወቁ ናቸው፡፡


6፡59 – የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት

አቶ አስጨናቂ ለማ (ሰብሳቢ)

ኢንጅነር ጌታሁን ሁሴን (ምክትል ሰብሳቢ)

አቶ መሃመድኑር አብድልከሪም አባል)

ወ/ሮ ህይወት አዳነ (አባል)

አቶ ኢብራሂም አደም (አባል)

ሌሎቹ አንደተሰጣቸው ድምፅ ተጠባባቂ ሁነዋል፡፡


6፡58 – የአስመራጭ ኮሚቴ እጩዎች እና ያገኙት ድምፅ

126 – አቶ አስጨናቂ ለማ

101 – አቶ መሃመድኑር አብድልከሪም

70 – አቶ ኢብራሂም አደም

63 – አቶ ጌታቸው አበራ

108 – ኢንጅነር ጌታሁን ሁሴን

76 – ወ/ሮ ህይወት አዳነ

53 – አቶ ሰለሞን ሎሀ

43 – አቶ እስክንድር ጀምበሬ


6፡49 – አንድ የጠቅላላ ጉባኤ አባል አምስት ግዜ ድምፅ መስጠት ይችላል፡፡


6፡48 – ወደ አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ አልፈናል፡፡


6፡41 – ለአስመራጭ ኮሚቴ እጩ ሆነው የቀረቡት ግለሰቦች ራሳቸውን ለጠቅላላ ጉባኤው እያስተዋወቁ ይገኛል፡፡


6፡31 – የአስመራጭ እና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ እጩዎች

አስጨናቂ ለማ (የስፖርት ሳንይንስ እና ማኔጅመን ዲግሪ ያላቸው በተለያዩ ቦታዎች የሰሩ)

መሃመድኑር አብድልከሪም (የህግ ዲግሪ ያላቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት የነበሩ አሁን ዳኛ እና ጠበቃ)

ኢብራሂም አደም (በአስተዳደር አድቫንስ ዲፕሎማ ያላቸው በንግድ ስራ የተሰማሩ ወጣት የስፖርት ባለሙያ)

ጌታቸው አበራ (በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ዓቃቤ ህግ እና ጠበቃ ሆነው እያገለገሉ ያሉ)

ኢንጅነር ጌታሁን ሁሴን (በሲቪል ኢንጅነር፣ ፓለቲካል ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዲግሪ እና በዓለም አቀፍ ንግድ ማስተርስ ያላቸው በተለያዩ ሃላፊነቶች ያገለገሉ)

ህይወት አዳነ (በቋንቋ ዲግሪ ያላቸው በአፍሪካ ህብረት እየሰሩ የሚገኙ)

ሰለሞን ሎሃ (በባይሎጂ ዲግሪ መምህርነት ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ)

እስክንድር ጀንበሬ (እጩ ዶክተር በስርዓተ ትምህርት እና ማስተማር ድግሪ በመምህርነት ሙያ እያገለገሉ ያሉ)


6፡29 – ወደ ሁለተኛው አጀንዳ ጠቅላላ ጉባኤው አልፏል፡፡ አምስት አባላት ያሉትን የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትን ለመምረጥ ዕጩዎች ይቀረባሉ፡፡ ስምንት እጩዎች ለአስመራጭ ኮሚቴ አሉ፡፡ የእጩዎችን ሲቪ ዋና ፀሃፊው አቶ ሰለሞን ያቀርባሉ፡፡


6፡28 – አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ከእረፍት ተመልሷል


5፡52 – 109 ድጋፍ እና በ9 ድምፅ ተአቅቦ መመሪያው ፀድቋል፡፡


5፡51 – ፊፋ የላከውን የምርጫ መመሪያ ለማፅደቅ ድምፅ ቆጠራ እየተካሄደ ነው፡፡


5፡50 – ፊፋ መመሪያውን ብዙም ባታሻሽሉት ብሎናል፡፡ ስለዚህም እባካችሁ ያልገባችሁን እናስረዳለን ግን አሁን ብናፀድቀው ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ለሁሉም ሰው እድል ሰጥቻለው፡፡ ፕሬዝደንት ጁነይዲ


5፡47 – በቃላት ዙሪያ ያሉትን ግድፈቶች ለማረም እንዲያውም በሁለት ትርጉም ቤቶች ነው ያስተረጎምነው፡፡ ማረም ያለብን የቃላት ግድፈቶች ልክ ነው ይታረማሉ፡፡ ዋና ፀሃፊ አቶ ሰለሞን


5፡44 – የስነ-ስርዓት ስህተቶችን እያየው ነው፡፡ ይሄ አስፈላጊ አይደለም፡፡ አንቀፅ 8 እና 20 ይጋጫሉ፡፡ ይሄ እንዴት ሆነ? አንቀፅ 21 የተባሹ ተቀባይነት የሌለው ይላል፡፡ ምን ማለት ነው?


5፡37 – የአማርኛው መመሪያ የቃላት ግድፈት አለባቸው፡፡ አንዳንድ አንቀፆች የአማርኛው ቃል ስለሚጣፍጥ ብቻ የገቡ ናቸው፡፡ ደንብ ግልፅ መሆን ይገባዋል ግራ ማጋባት የለበትም፡፡ የቤት ውስጥ ደባል፣ እህት፣ ወንድም፣ ትዳር አጋር የሚሉ ቃላት አሉበት፡፡ ምንድነው ይሄ? አፊኒየት እና ተባባሪ አንድ ቃል አይደለም፡፡ ጥያቄ እና ጥቆማ ይለያያል፡፡ ገፅ 5 ላይ ውሳኔዎችን በተመለከተ ግድፈቶች አሉበት፡፡ አንቀፅ 13 የሚገርም ነው ይፋው ደንብ ስርጭት ይላል ይሄ የተረጎመው ሰው ቢመልስ ደስ ይለኛል፡፡ አቶ ነዋይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ


5፡33 – አንድ ነገር መናገር እፈልጋለው የቡና ደጋፊ እና የቡና ባለድርሻ የተለያየ ነው፡፡ ይህንን እወቁ አቶ ጁኒየዲ፡፡ ፊፋ ፊፋ እያላችሁ አታውሩ፡፡ እናንተ ስራችሁን በአግባቡ ብትሰሩ ፊፋ ምናም አትሉም ነበር፡፡ አንቀፅ 2 መ የስራ አስፈፃሚው ሌላ ተመራጭ እስከመጣ መቀጠል አለበት ይላል፡፡ ችግሩ እረሶ አቶ ጁኒየዲ እራሱ ተወዳዳሪ ኖት፡፡ ከእርሶ በተጨማሪ ሌሎች መምሪያ ሃላፊዎችም ተወዳዳሪዎች ናችሁ፡፡ ይህ ዴሞክራሲ አይደለም፡፡ የተወዳደራችሁት ወረዱ እና እንሂድ፡፡ ስለዚህ ይህ አንቀፅ መሰረዝ አለበት፡፡ በአንድ ጎን ተወዳዳሪ ናችሁ የማይወዳደሩት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይቀጥሉ የምትዋደሩት ወረዱ ነው የምለው፡፡ ይሄ ለምርጫ ይቀረብልኝ፡፡ መቶ አለቃ ፈቃደ ከኢትዮጵያ ቡና


5፡28 – ስላለፈ ጉዳይ እያወራን ለምን ለእግርኳሱ ፋይዳ የሌለው ነገር ላይ ሰዓት መግደሉ ጥቅሙ አይታየኝም፡፡ የፊፋ አባል እስከሆንን ደረስ ፊፋ ለሚያወጣው ሮድ ማፕ ተገዢ መሆን አለብን፡፡ በራሳችን እንሂድ ከተባለ ፊፋ ይቀጣናል፡፡ ፊፋ ይህን መንገድ ተከትሉ ብሎናል፡፡ መስተካከል ያለባቸው አንቀፆች በሰነከ ሁኔታ መወያየት ያስፈልጋል፡፡ ዋና ፀሃፊው በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ያለውን ሚና በሚገባ ተቀምጧል፡፡ ምርጫውን የሚጠራው ማነው የሚለውም በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ዋና ፀሃፊ አቶ ሰለሞን


5፡20 – አንድ ተወዳዳሪ ለቅሬታ ሰሚ ይገባኝ ማለት ይችላል፡፡ ለመንግስት አይደለም፡፡ እኛስ ምን አደረግን፡፡ ጥር 13 መደረግ የሚችል ምርጫ አንዳንድ ሰዎች ፊፋ ይቀጣናል እያሉ ደብዳቤ እየፃፉ ነገሮችን አበላሽተዋል፡፡ የአስፈፃሚ ኮሚቴ ሊቀ መንበሩ ሃላፊነት ካልታወቀ በኃላ ላይ ፊፋ ይቀጣል ካፍ ይቀጣናል እየተባለ ወደ ችግሮች ውስጥ እንገባለን፡፡ እኛ ካርዶችን አትመን ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ጨርሰን ነበር ሆኖም ጉባኤው ይወስን ተብሎ ቀኑ ተራዘመነ፡፡ (አቶ አባዲ ወደ ኃላ እየተመለሱ ስለሆነ በማለት አቶ ጁኒየዲ አቋርጠው ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል)፡፡ አቶ አባዲ የቀድሞ የምርጫ አስፈፃሞ ኮሚቴ አባል


5፡16 – ከዚህ ጉባኤ ላይ የሚነሱ አንዳንዳ ሃሳቦች ያስገርማሉ፡፡ መንግስት ትክክል ነው አያገባውም ግን ፊፋ አያገባውም ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስረዱኝ እስቲ ፊፋ ነው የእግርኳስ የበላይ አካል እንዴት አያገባውም? አንቀፅ 9 ላይ የተገለፀውን አንደገና መታየት አለበት፡፡ አቶ ሰለሞን ያነሱትን ሃሳብ እቀበላለው፡፡ አቶ ኢሳያስ ከጅማ አባ ጅፋር


5፡13 – እዚህ የተገኘነው አስመራጭ ኮሚቴ ለመምረጥ ነው፡፡ ወደ ሌሎች ጉዳዮች እየገባን እያንዛንዛን መሄድ ለምን ያስፈልጋል፡፡ መመሪያው በአማርኛ ተፃፈ በእንግሊዘኛ ምንም የተለየ ነገር የለውም፡፡ ፊፋ በእንግሊዘኛ የላከልን የእንግሊዘኛ ተጋናሪ ውስጥ ስለምንመደብ ነው፡፡ የፊፋ ዱላ ሊያርፍብን እንግባ፡፡ እዚህ የተገኘውን ጉዳይ ላይ እናተኩር፡፡ አቶ ሰለሞን አባተ ከአዲስ አበባ አሰልጣኞች ማህበር


5፡04 – የተነሳው ጥያቄ ልክ ነው እንመልሳለን፡፡ ይህ መመሪያ ለአሁን ምርጫ ለማስፈፀም ነው እንጂ ፊፋ እንዳለው ችግሮች ስላሉብን የተሻለ መመሪያ ለቀጣይ ግዜ እናደርጋለን፡፡ የስልጣን ግዜን በተመለከተ ከዚህ በፊት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ምርጫው ሲራዘም መቀጠል ትችላላችሁ ተብሎ ነበር፡፡ ለዚህም ማስረጃ አለኝ፡፡ ምርጫው ስለተራዘመበት ጉዳይ በሚዲያም ብዙ ተብሏል ግዜ ወስጄ እዚህ ላይ መናገር እፈልጋለው፡፡ በኢትዮጵያ ገና ወቅት ምርጫ ሊካሄድ ነበር ሆኖም መራዘም ነበረበት ተራዘመ፡፡ የቻን ውድድር ስለነበር በፊፋ እና ካፍ ጥያቄ መሰረት ተራዘመ፡፡ በሌላኛው ቀን የሰጠነው ቀጠሮ ላይ ካፍ ሰው ላከ ፊፋ ሳይልክ ቀረ፡፡ ስለዚህም ለፊፋ ፅፈን ምርጫውን እንድናካሄድ ጠየቅን፡፡ መጋቢት ላይ ፊፋ ታዛቢ ልኮ ሁሉንም መረመር አሁን ላይ ያለው ነገር ወሰነ፡፡ መቶ አለቃ ፈቃደ ብዙ ግዜ አያለው ሙሉ ስታዲየም የሚገኘው የቡና ደጋፊ ውረድ ይለሃል ግን ትወርዳለህ ወይ 40 ዓመት በቃህ እያሉ ነው፡፡ አትወርድም ምክንያም ሁሉም በስርዓት ስለሚሆን፡፡ (በመቶ አለቃ ፍቃደ ሃሳብ ለመስጠት ያቀረቡት ጥያቄ በፕሬዝደንቱ ንግግረ መቀጠል ምክንያት ተቋርጧል)፡፡ እኛም ሰልችቶናል ይህ መታወቅ አለበት፡፡ ፕሬዝደንት ጁኒይዲ


5፡01 – ፊፋ ከዚህ በፊት እየተኬደበት የነበረው መንገድ ልክ አይደለም ብሎ ይህንን መመሪያ አቅርቧል፡፡ የተቀመጠው ሰነድ ትክክል ነው አይደለም የሚለው ላይ እንወያይ፡፡ እንዴት አዲስ መመሪያ ይወጣል ብሎ መጠየቅ ምን ይባላል፡፡ ከስብሰባ በፊት ሁሌም ተዘጋጅተን መምጣት አለብን፡፡ አቶ ነዋይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ


4፡56 – ስህተትን በስህተት እያረምን ወደ ማንወጣው አዝቅጥት ውስጥ እየገባን ነው፡፡ የአሁኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤው የሰጣችሁ ሃላፊነት ለአራት ዓመት ብቻ ነው፡፡ እናንት እዚህ ቆይታችሁ መመሪያውን ለማፅደቅ ምንም ዓይነት ስልጣን የላችሁም ስለዚህም ይህንን ምታደርጉ ከሆነ ስህተትን በስህተት እያረምን የምንሄደው፡፡ ሀሳቦች አይገደቡ፡፡ በሀሳቦች እንፋጭ የተሻለ ነገር ይመጣል፡፡ ህግ እና ስርዓትን ሳንከተል ከሄድ ወደ ባሰ ችግር እንገባለን፡፡ ፊፋ እርዳታ አቅርቧል እናመሰግናለን ግን ጂኒየዲ ይቀጥል አላለም፡፡ ይህን ጠቅላላ ጉባኤውን መወሰን የላበት፡፡ አቶ ገዛኸኝ ከአዲስ አበባ ከተማ


4፡54 – መመሪያው የትርጉም ክፍል የለውም፡፡ ይህ ሊኖር በተገባ ነበር፡፡ አንዳንድ አንቀፆች ጠርተው አልተገለፁም፡፡ ለምሳሌ አንቀፅ 3 የአስመራጭ ኮሚቴን ማቅረብ ይላል ሆኖም ማነው የሚቀርባቸው፡፡ ተወዳዳሪዎች ይላካሉ ይላል ማነው የሚልካቸው፡፡ ይህ መገለፅ አለበት፡፡


4፡49 – እኔ ዛሬ የመጣሁት ምርጫው ተካሂዶ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ይኖራል ብዬ ነበር፡፡ የምርጫ ማስፈፀሚያ መመሪያውን ለማፅደቅ እናንተ ተመራጭ ሆናችሁ ማነው ስልጣን የሰጣችሁ


4፡47 – የምርጫው መመሪያው ከ15 ቀን በፊት የተላከው በእንግሊዘኛ ቋንቋ፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም፡፡ ስለመንግስት ጣልቃ ገብነት ተነስቷል፡፡ ብዙዎቹ ክለቦች በመንግስት ስር ነው ያሉት ይህንን ተሳቢ ያደረገ ቢሆን መልካም ነው፡፡


4፡27 – የአስመራጭ ኮሚቴው አምስት አባላት ይኖሩታል፡፡


4፡19 – የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን የፕሬዝደንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ ኮድ በዋና ፀሃፊው ሰለሞን ገብረስላሴ እየቀረበ ይገኛል፡፡ መመሪያው 6 ክፍሎች እና 27 አንቀፆች አሉት፡፡


4፡11 – ቃላ- ጉባኤ የሚይዙ ሶስተ ሰዎች ተመርጠዋል፡፡ ተድላ ዳኛቸው፣ሳራ ሰዒድ እና የሺዋስ በቀለ ቃለ-ጉባኤ ለመያዝ ጋሻው ረታ እና ጌታቸው ገብረማሪያም ድምፅ ቆጣሪ ሆነዋል፡፡


3፡59 – የፊፋ ተወካይ ሚስተር ዴቪድ ፋኒ

ይህ የእናንተ ስብሰባ ነው፡፡ እዚህ የተገኘሁት ጠቅላላ ጉባኤውን ለመታዘብ ነው፡፡ ሶስት አጀንዳዎች ብቻ እዚህ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ መነሳት አለባቸው፡፡ የምርጫ ኮድ ማፅደቅ፣ የምርጫ አስፈፃሚ እና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መምረጥ ነው፡፡ የአትዮጵያ እግርኳስ ባለፉት ወራት ብዙ ችግሮችን አይቷል ሆኖም በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ መነሳት ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ ብታተኩቱ እመክራለው፡፡ አዲሱ አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን ይመጣ እና አዲስ ስራ አስፈፃሚ ይመረጣል፡፡ የምርጫው ቀን አስቀድሞ ለፊፋ ይላካል፡፡ ከዛም ነው የፊፋን አዎንታዊ ምላሽ ሲያገኝ የምርጫ ስርዓቱ የሚቀጥለው፡፡ ጥያቄዎች ይኖራሉ እኔም እንዲኖሩ እፈልጋለው ምክንያቱም ሁሉም ነገሮች መጥራት አለባቸው፡፡ ከዚህ ጠቅላላ ጉባኤ በኃላ ለፊፋ የተፈጠረውን ሁሉ ሪፖርት አደርጋለው፡፡


3፡54 – አጀንዳዎቹን አሳውቀናል፤ ሁለት ናቸው፡፡ ፊፋ ያስቀመጠልን መንገድ አለ፡፡ የምርጫ አካሄዳችሁ ጠንካራ አይደለም ተብለናል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አስመራጭ ኮሚቴ እንድትመርጡ በህጉ መሰረት የሚል ነው፡፡ በሰላም ስብሰባው እንዲጠናቀቅ ህጉን ተክትሎ እንዲሄድ ያስፈልጋል፡፡ ጭቅጭቆች እና ንትርኮች አስፈላጊ አይደሉም አሁን፡፡ ቡዙ መባል የሚችል ነገር አለ ግን ሁሉንም ካወራን ግዜ አይበቃንም ስለዚህም ዋናው ጉዳይ ላይ ሃሳባችን ብንሰጥ፡፡ አምባገነን ለመሆን ሳይሆን ከተቀመጠው አጀንዳ ውጪ ሌላ ማስያዝ አይቻልም፡፡ አቶ ጁኒይዲ


3፡52 – የፌድሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ጁኒየዲ ባሻ የመክፈቻ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡


3፡49 – ድምፅ መስጠት የሚችሉ 122 ክለቦች በጠቅላላ ጉባኤው ተገኝተዋል፡፡ በፌድሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 20 እንደሚያስቀምጠው መሰረት የምዕላተ ጉባኤው መሟሏቱ ተረጋግጧል፡፡


3፡38 – አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው ተጀምሯል፡፡ ምልዐተ ጉባኤ መሟላቱን እና ቃለ-ጉባኤ ያዥና ድምፅ ቆጠራያዎችን ይሰየማሉ፡፡ የፌድሬሽኑ ዋና ፀሃፊ አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ የመክፈቻ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡


3፡25 – የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ሊጀመር ጥቂት ደቂቃዎች ቀርተዋል፡፡ ዛሬ የሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች የሆኑት የምርጫ ማስፈፀሚያ መመሪያን ማፅደቅ፣ የምርጫ አስመራጨ ኮሚቴና የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ ነው፡፡ ቦትስዋናዊው የፊፋ ተወካይም ጠቅላላ ጉባኤውን ለመታዘብ ተገኝተዋል፡፡