የአበባው ቡታቆ ማረፍያ አርባምንጭ ሆኗል

አርባምንጭ ከነማ ከ ሱዳን መልስ ክለብ አልባ ሆኖ የቆየው አበባው ቡታቆን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ አበባው ከሱዳኑ አል-ሂላል ከተመለሰ ወዲህ ስሙ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አዳማ ከነማ ፣ ሲዳማ ቡና እና ዳሽን ቢራ ጋር ሲያያዝ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ተጫዋቹ ለትውልድ ከተማው ክለብ ለመጫወት 1.8 ሚልዮን ብር በ2 አመት ውስጥ ሊከፈለው ተስማምቷል፡፡ (በወር 75 ሺህ ብር) ይህም የሃገራችን ከፍተኛው ደሞዝ ተከፋይ ያደርገዋል፡፡ ተጫዋቹ በጥቂት ቀናት ውስጥ ፌዴሬሽን ተገኝቶ ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አበባው ቡታቆ የተወለደው በአርባምንጭ ከተማ ሲሆን አሁን ለፈረሰው ዝነኛው አርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ክለብም ተጫውቷል፡፡ አርባምንጭ ከነማ ከአበባው በተጨማሪ ከብሄራዊ ሊጉ 2 ተጫዋቾችን ለማስፈረም መስማማቱ ተነግሯል፡

ያጋሩ