የበረከት ይስሃቅ ማረፍያ ደደቢት ሆኗል

የመብራት ኃይሉ ድንቅ አጥቂ በረከት ይስሃቅ ለደደቢት ለመጫወት ተስማምቷል፡፡ የአጥቂው ስም ከበርካታ ክለቦች ጋር ተያይዞ የነበረ ሲሆን መብራት ኃይልን ጨምሮ በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ዳሽን ቢራ ፣ ንግድ ባንክ እና መከላከያ ሲፈለግ ቆይቷል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የአጥቂ መስመር አማራጮች ጠበውበት የነበረው ደደቢት የበረከት ይሳቅን መፈረም ተከትሎ የፊት መስመሩ ይጠናከራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በረከት የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው በ2001 አም. በሀዋሳ ከነማ ነው፡፡ በሀዋሳ ተስፈኛ ተጫዋችነቱን ያስመሰከረው በረከት በ2005 ወደ መብራ ኃይል ከተዛወረ ወዲህ ከፍተኛ መሻሻል በማሳየት ተከላካዮችን ከሚያሸብሩ ተጫዋቾች አንዱ ሆኗል፡፡

ደደቢት የናይጄርያዊውን ሳሚ ሳኑሚ ዝውውር ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ያጋሩ