የካፍ ኢንስትራክተር አብርሃም ተ/ኃይማኖት ሁለተኛ መፅሃፋቸውን ሊያስመርቁ ነው

ከክለብ ደረጃ አሰልጣኝነት ከራቁ በኋላ በአዲስ አበባ እና መቐለ በጀመሯቸው የህፃናት እና ወጣቶች የእግር ኳስ ትምህርት ቤት ላይ እየሰሩ የሚገኙት አሰልጣኝ አብርሀም ተክለኃይማኖት ” እግርኳሳችን እና የኃሊት እርምጃው” የተሰኘ 2ኛ መፅሃፋቸውን ሰኔ 3 በአዲስ አበባ እንዲሁም ሰኔ 9 በመቐለ ከተሞች እንደሚያስመርቁ ተገልጿል።

ስለ መፅሃፉ እና ተያያዥ ገዳዮች አሰልጣኝ አብርሀም ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

*ስለ መጀመርያው መፅሃፍ

በመጀመርያ መፅሃፌ ያገኘሁት የህዝብ ምላሽ በጣም ከጠበቅኩት በላይ ነበር። በተለይም የባለሙያዎች አስተያየት የሚያበረታታ ነበር ፤ ሆኖም እንደዚህ አይነት መፅሃፎች በሀገራችን ስላልተለመዱ በገቢ በኩል ብዙም ተጠቃሚ አልሆንኩም።

*ስለ አሁኑ መፅሃፍ ይዘት 

ከመጀመርያው መፅሀፌ ብዙ ልዩነት አለው። የመጀመርያው መፅሃፌ በአሰልጣኞች ሚና ፣ በስነ-ልቦና ፣ በታዳጊዎች ልማት እንዲሁም ላለው ከፍተኛ የአመራር ችግር የሚሰጡ የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ያተኮረ ነበር። የአሁኑ ግን የተለየ ይዘት ያለው ነው።

* ስለ ቀጣይ ዕቅድ

በቀጣይ የጀመርኳቸውን የህፃናት እና ወጣቶች ፕሮጀክቶች በማስፋት መሰረቱ የተናጋው የሀገራችን እግር ኳስ ላይ ብዙ መስራት እፈልጋለው። በመቐለ እና አዲስ አበባ የጀመርኳቸው ፕሮጀክቶች በወላጆች ጥሩ ተቀባይነት አግኝተዋል። በመቐለ ላጋጠመን የሜዳ ችግርም የከተማው መስተዳድር እና የመቐለ ዩኒቨርስቲ ችግራችን ለመፍታት ተስፋ  ሰጪ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
በመጨረሻም የመጀመርያውንም ሆነ እና የአሁኑን መፅሃፎቼን ሳሳትም ዕገዛ ያደረጉልኝ የሁልጊዜ ተባባሪዎቼ ተ/ብርሃን አምባየ ኮንስትራክሽን እና ጃዕፋር መፅሃፍት መደብርን ማመስገን እፈልጋለው።

የመጀመርያው መ

መጽሀፍ