መከላከያ ጀማል ጣሰው እና መሃመድ ናስርን አስፈረመ

መከላከያ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር መስማማት ያልቻለው ጀማል ጣሰው እና ከመድን ጋር የተለያየው መሃመድ ናስርን አስፈርሟል፡፡

ጀማል ጣሰው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በኮንትራት ማራዘምያ ዙርያያደረገው ድርድር ካለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ለመከላከያ ፊርማውን አኑሯል፡፡ ጀማል ኢትዮጵያ ቡና እዲከፍለው የጠየቀው ገንዘብ በክለቡ ተቀባይነት ያጣ ሲሆን ቡና ያቀረበውን 650ሺህ ብር ጀማል ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡

የቀድሞው የሀዋሳ ከነማ እና ደደቢት ግብ ጠባቂ ከመከላከያ ጋር ለሁለት አመታት ለመጫወት የተስማማ ሲሆን 750 ሺህ ብር ተከፍሎታል፡፡

ሌላው ለመከላከያ የፈረመው መሃመድ ናስር የመድንን መውረድ ተከትሎ ከተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጋር ድርድር ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል፡፡ መሃመድ ከሱዳን ከተመለሰ በኋላ በመድን ግማሽ የውድድር ዘመን ያሳለፈ ሲሆን ስሙ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና የአረብ ሃገራት ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቆይቷል፡፡

:

:

ምንጭ – ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ (ሬድዮ)

ምንጭ – ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ (ሬድዮ)

ያጋሩ