የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ ትላንት በተካሄዱ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቀጥሏል። በምድብ ሀ መሪዎቹ አቻ ሲለያዩ በምድበ ለ ሀዋሳ በግስጋሴው ቀጥሏል።
በምድብ ሀ መድን ሜዳ ላይ መሪው ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮጵያ መድን ባደረገው ጨዋታ 2-2 ተለያይቷል። ቡናዎች ከመከ2-0 መመራት ተነስተው ነው አቸ መለያየት የቻሉት። ወደ አሰላ የተጓዘው ተከታዩ መከላከያ ከጭላሎ ጋር በተመሳሳይ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቶ ከመሪው ያለውን ልዩነት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
የሁለት ሳምንት እድሜ በቀረው ምድብ ሀ ከተከታዩ በ5 ነጥቦች የራቀው ኢትዮጵያ ቡና ቀጣዩን ጨዋታ ማሸነፍ የምድቡ አሸናፊነትን እንዲያረጋግጥ ይረዳዋል።
የምድብ ሀ ውጤቶች እና ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል፡-
በምድብ ለ አሌክትሪክን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 3-0 በመርታት መሪነቱን አጠናክሯል። ማራኪ እና ጥሩ የኳስ እንቅስቃሴን በተመለከትንበት ጨዋታ 8ኛው ደቂቃ ላይ አቤል ካሳ አመቻችቶ የሰጠውን ኳስ የግራ ተከላካዩ እና የቡድኑ አምበል ጌታሁን አየለ አስቆጥሮ ሀዋሳን ቀዳሚ አድርጓል። 44ኛው ደቂቃ ላይ በግራ መስመር ቴዎድሮስ መሐመድ የሰጠውን ኳስ ወንድማገኝ ታደሰ አስቆጥሮ በሀዋሳ 2-0 መሪነት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜም በርካታ የግብ አጋጣሚን በመፍጠሩ ረገድ ባለሜዳዎቹ ሀዋሳዎች የተሻሉ ነበሩ። ሀዋሳዎች ሁለት ጊዜ በቴዎድሮስ መሀመድ እና አቤሴሎም አፈወርቅ አማካኝነት ግብ ቢያስቆጥሩም የእለቱ ዳኛ ግቦቹን የሻሩበት መንገድ በርካቶችን ለተቃውሞ የገፋፋ ሲሆን 86ኛው ደቂቃ ላይ ያሬድ መሐመድ በቅብብል ከሐብታሙ ጋር ተጫውቶ ወደ ሳጥን ይዘው ገብተው በመጨረሻም ሐብታሙ መኮንን ከመረብ አሳርፎ ሀዋሳ ከተማ 3-0 አሸናፊ ሆኗል፡፡
በዚሁ ምድብ ወላይታ ድቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ነግብ ተጋርቶ ከመሪው ያለውን ልዩነት ሲያሰፋ ደደቢት በታዲዮስ ሐት-ትሪክ ታግዞ ሲዳማ ቡናን 3-0 አሸንፏል።
ሊጠናቀቅ ሁለት ሳምንት በቀረው በዚህ ምድብ አደድ ጨዋታ የሚቀረው ሀዋሳ ከተማ ከጨዋታው አንድ ነጥብ ለምድብ አሸናፊነቱ በቂ ነው።