የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምርጫ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

04:58 የወቅቱ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አስረክበዋል።

ኮ/ል አወል አብዱራሂም ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው በ44 ድምፅ ተመርጠዋል።
04:10 የምክትል ፕሬዝዳንት ምርጫው ተጀምሯል።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት

1 ሶፊያ አልማሙን

2 አበበ ገላጋይ

3 አሊሚራህ መሐመድ

4 ሰውነት ቢሻው

5 ዘሪሁን ቀቀቦ

6 ኮ/ል አወል አብዱራሂም

7 አብዱራዛቅ ሀሰን

8 ዮሴፍ ተስፋዬ

9 ቻን ጋትኮት

10 ኢብራሂም መሐመድ

* በውጤቱ መሰረት ቻን ጋትኮች፣ ዮሴፍ ተስፋዬ እና ኢብራሂም መሐመድ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ውስጥ ተካተዋል።

የድጋሚ ምርጫ ውጤት 

ቻን ጋትኮት – 80

ዳግም ምላሸን – 3 

ዮሴፍ ተስፋዬ – 65

ኃይለየሱስ ፍስሃ – 41

ተስፋዬ ኦሜጋ – 23

ኢብራሂም መሐመድ – 75

03:20 የድጋሚ ምርጫው ውጤት ተቆጥሮ አልቋል። 136 ድምፆች ተቆጥረዋል።

* የጋምቤላ የሐረሪ እና የአዲስ አበባ ምርጫዎች በድጋሚ እየተደረጉ ይገኛሉ። አስራት ኃይሌ በምርጫው ሒደት ብስጭታቸውን ገልፀው ከድጋሚ ምርጫው ራሳቸውን አግልለዋል።

* በፕሬዝዳንታዊ ውድድሩ ላይ ያለው የ50+1 ህግ በስራ አስፈፃሚ ምርጫ ላይም መኖር አለበት በሚል ከአዲስ አበባ በተነሳው ተቃውሞ መሰረት ይህንን ያላሟሉ ክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች ምርጫ በድጋሚ ይደረጋል።

ይፋ የተደረጉ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት

1 ሶፊያ አልማሙን

2 አበበ ገላጋይ

3 አሊሚራህ መሐመድ

4 ሰውነት ቢሻው

5 ዘሪሁን ቀቀቦ

6 ኮ/ል አወል አብዱራሂም

7 አብዱራዛቅ ሀሰን

ቆጠራው ተጠናቆ ያገኙት ድምፅ እየተገለፀ ይገኛል

ሶፊያ አልማሙን – 114

አወል አብዱራሒም – 101

ዘሪሁን ቀቀቦ – 96

አበበ ገላጋይ – 89

አሊሚራህ መሐመድ – 83

ሰውነት ቢሻው – 81

አብዱራዛቅ ሀሰን – 72

ቻን ጋትኮት- 66

ዮሴፍ ተስፋዬ – 63

ኃይለየሱስ ፍስሃ – 61

ሲራክ ኃይለማርያም (ዶ/ር) – 61

ወገኔ ዋልንጉስ (ዶ/ር) – 57

ኢብራሂም መሐመድ – 55

ሙራድ አብዲ – 50

ተስፋዬ ኦሜጋ – 43

ኡቻላ ኡጁሉ – 41

ወንድአወቅ አበዜ – 33

ወልደገብርኤል መዝገቡ – 26

አስራት ኃይሌ – 25

ዳግም ምላሸን – 19

12:20 – የስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ ድምፅ ቆጠራ እየተካሄደ ነው።


10:45 አቶ ኢሳይያስ ጂራ 87 ድምፅ በማግኘት ምርጫውን ሲያሸንፉ አቶ ተካ አስፋው ቀሪውን 58 ድምፅ አግኝተዋል።  
10:38 የድጋሚ ምርጫው ቆጠራ ተካሂዷል።

09:53 የድጋሚ ምርጫው ሒደት እየቀጠለ ነው።

09:40 የደቡብ እና ኦሮሚያ ክለቦች እና ፌዴሬሸኖች በመቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ እና አቶ ሚካኤል አምደመስቀል አግባቢነት በድጋሚ ወደ አዳራሹ ገብተዋል።

9:28 የኦሮሚያ እና ደቡብ ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች እና በስራቸው የሚገኙ ክለቦች እንዲሁም አቶ ኢሳይያስ ጂራ የስብሰባ አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል።

9:25 አቶ ተስፋይ እና አቶ ጁነይዲ ከድጋሚ ምርጫው ራሳቸውን አግልለዋል።

9፡21 – ” ህጉ እንደማያሰራ እያወቁ ማሻሻያ ያላደረጉ ሰዎች ተጠያቂ ናቸው፡፡ ከዙሪክ አውቶማቲካሊ ነው ውድቅ የሚያደርጉን፡፡ አጥፍተን ከሆነ ይቅርታ አድርጉልን፡፡ ወደ ምርጫ እንሂድ፡፡ ” የአስመራጭ ኮሚቴ አባል  

9፡16 –  ” ያፀደቃችሁንት የ2014 ድንብ መከተል አለባችሁ፡፡ ከ50 ሲደመር አንድ በላይ ድምፅ ካላገኘ ተወዳዳሪው ማሸነፍ አይችልም፡፡ በድጋሚ ምርጫ ግን አብላጫውን ድምፅ ያገኘ ማሸነፍ ይችላል፡፡ ይህ ካልሆነ ካይሮ እና ዙሪክ ላይ ሪፖርት የምናደርገው ይህንን ነው፡፡ ” ሚስተር ሉካስ ከፊፋ

9፡12 – ” ሁላችንም በህግ እና ስርዓት ነው መናገር ያለብን፡፡ እኛ ህጉን ተከትሎ ብላችሁን ነው የመረጣችሁን አሁን ደግሞ ህጉን እየከተልን ነው፡፡ ይህ ስብሰባ የምርጫ ስብሰባ እንጂ ውይይት አይደለም፡፡ ” የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ

9:10 – ” እኔ የፌደሬሽኑ ፕሬዝደንት ነኝ፡፡ የመብት ጥሰት ለመፈፀም ነው እንቅስቃሴ ያለው፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው የእኔን ፕሬዝደንትነት ያፀደቀበትን መንገድ ለፊፋ ማሳወቅ አለበት፡፡ እኔ አሁንም እናገራለሁ የፌደሬሽን ፕሬዝደንት ነኝ፡፡ ”  አቶ ኢሳያስ ጅራ

09:10 – ጉባዔው ከምሳ እረፍት ተመልሷል።

በምርጫው የተገኘው አብላጫ ድምፅ በቂ እንዳልሆነ እና 50+1 ድምፅ ማግኝት እንዳለበት የፊፋው ተወካይ ሚ/ር ሉካስ ገልፀዋል።

ምርጫው በድጋሚ የመካሄድ አለመካሄድ ጉዳይ ጉባዔተኛው ከምሳ ሲመለስ ይወሰናል። 

07:11 – የምሳ እረፍት 

6:44 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ቀጥሎ ይካሄዳል። ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ ከኦሮሚያ በመገኘታቸው ከኦሮሚያ የሚወዳደሩ እጩዎች በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውስጥ ቦታ አይኖረውም።



አቶ ኢሳይያስ ጂራ – 66 ድምፅ

አቶ ተካ አስፋው – 47 ድምፅ

አቶ ጁነይዲ ባሻ – 28 ድምፅ

ተስፋይ ካህሳይ – 3 ድምፅ

6፡27 – 145 ድምፆች መሰጠታቸው ተረጋግጧል፡፡

6፡16 – ድምፅ መስጠቱ አሁን ላይ ተጠናቋል፡፡ አሁን ወደ ድምፅ ቆጠራ የምናመራ ይሆናል፡፡

6፡10 – ማህበራት ድምፅ እየሰጡ ነው፡፡

5፡43 – የአንደኛ ሊግ ክለቦች ድምፅ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

5፡30 – የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ድምፅ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

5፡23 – የክልል እና የከተማ እግርኳስ ፌደሬሽኖች ተወካዮች ድምፃቸውን ሰጥተዋል፡፡ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ድምፅ አላቸው፡፡ አሁን የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ድምፅ እየሰጡ ነው፡፡

5፡09 – የፕሬዝደንታዊ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ እየተካሄደ ነው፡፡

የጋምቤላ እና የኢትዮ-ሶማሌ ክልል እግርኳስ ፌደሬሽኖች ድምፃቸውን ሰጥተዋል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እግርኳስ ፌደሬሽን ድምፅ አሁን ይሰጣሉ፡፡

05:07 ከሻይ እረፍት ተመልሰዋል። ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ቀጥሎ ይካሄዳል።


4፡23 – እጩ ተወዳዳሪዎች ያላቸውን ሃሳብ በሁለት ደቂቃ ውስጥ የማስተዋወቅ እድል ተሰጥቷቸዋል፡፡


4፡13 – የፕሬዝደንታዊ ምርጫ እጩዎች

አቶ ጁነይዲ ባሻ (ድሬዳዋ) – ማስተርስ ዲግሪ የአስተዳደር ምሩቅ

የሐረር ቢራ ክለብ መስራች እና ፕሬዝደንት የነበሩ

አቶ ተካ አስፋው (አማራ) – የህግ ምሩቅ

የፌደሬሽን ተቀዳሚ ፕሬዝደንት እና የካፍ ድስፕሊን ኮሚቴ አባል የነበሩ

አቶ ኢሳያስ ጅራ (ኦሮሚያ) – የመጀመሪያ ድግሪ በባይሎጂ

ወረዳ ስፖርት ዴስክ ሃላፊ፣ የጅማ ከተማ ክለብ ስራ አስኪያጅ እና የሰበታ ወጣቶች እና ስፖርት ሂደት ሃላፊ

አቶ ተስፋይ ካህሳይ (ትግራይ) – የአካውንቲግ ምሩቅ

በተለያዩ ባንኮች በሃላፊነት የሰሩ እና በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የቦርድ አባል የነበሩ


4፡09 – ጠቅላላ ጉባኤው አጀንዳ አስይዞ በምርጫው መመሪያ ላይ አስታየት መስጠት ህግ አይፈቅድም በሚል የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እየገለፁ ነው፡፡ አሁን የተወዳዳሪዎች ዝርዝር ፕሮፋይል ሊቀርብ ነው፡፡


3፡54 – የምርጫው ሂደት አቶ አስጨናቂ ለጠቅላላ ጉባኤ እያሳወቁ ይገኛሉ፡፡

ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት 10 ከየክልል አንድ ሰው ይወከላል፡፡ ከአንድ በላይ እጩዎች ያቀረቡ ክልሎች የተሻለ ድምፅ ያለው ይገባል፡፡

50 ሲደመር 1 በሚለው የመጀመሪያዎቹ የተሻለ ድምፅ ያላቸው ያልፉ እና የተቀሩት እኩል ድምፅ ካገኙ ወደ ሁለተኛ ምርጫ ያልፋሉ፡፡

ፕሬዝደንት ሆኖ ያስመረጠ ክልል ካለ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውስጥ ተወዳዳሪ ቢኖረውም ኮታውን ይያዛል፡፡

በመጀመሪያው ዙር 10 ከ50% በላይ ካልሆኑ ለሁለተኛው ምርጫ ካርድ ተዘጋጅቷል፡፡

ለመምረጥ ወደ ሚስጥር ሳጥኑ ሲገቡ የሞባይል ስልክ መያዝ አይቻልም፡፡

ውክልና ያላመጣችሁ በዚህ ውድድር እና ምርጫ ላይ መሳተፍ አትችሉም፡፡

አንቀፅ 20 ስለድምፅ ቆጠራ ላይ የሚኖሩት እና የሚገኙት አስመራጭ ኮሚቴው አባላት ብቻ ናቸው፡፡

ቆጠራው እንደተጠናቀቀ በይፋ ውጤቱን ለጠቅላላ ጉባኤው ያሳውቃል፡፡


3፡49 – ” ለእኔ በእዚህ የጠቅላላ ጉባኤ ለመታዘብ ፊፋን በመወከሌ ደስተኛ ነኝ፡፡ በሰማራ በተደረገልኝ አቀባበል በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ይህ ምርጫ ስርዓት ተጓቷል፡፡ የፊፋ ታዛቢ አካል ወደ አዲስ አበባ መጋቢት ላይ መጥቶ ያሉትን ነግሮች አይቶ እና መርምሮ አቅጣጫ አሳይቷል፡፡ ፊፋ ምርጫው በፌድሬሽኑ መተዳደሪያ መሰረት እንዲደረግ መመሪያ ሰጥተናል፡፡ በልማት ስራዎች ብቻ ሳይሆን እግርኳሱን የሚጠቅም ደንቦች ላይም በጋር መስራቱን ይቀጥላል፡፡ አምሰግናለው መልካም እድል ለተወዳዳሪዎች፡፡ ” የፊፋ ተወካይ ሉካስ ኒኮላ


3:45 – በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስት በቅርበት ግዜያት ውስጥ የተፈጠሩ ችግሮችን እና የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለቶችን በህግ፣ በስርዓት እና በደንቡ መሰረት ለመፍታት ሁላችንም ሃላፊነት አለብን፡፡ ለዚህ ምርጫ መሳካት ሲሰሩ የነበሩ አካላቶችን በሙሉ አመስግናለው፡፡ ወ/ሮ ፈሪሃ


3፡42 – የዕለቱ የክብርት እንግዳ የኤፌድሪ ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ ፈሪሃ ንግግር እያደረጉ ነው፡፡


3፡39 – ቃለ ጉባኤ የሚይዙ ተጠቁመዋል፡፡
አቶ ጋሻው ረታ
አቶ ዳንኤል ዘለቀ
አቶ ነብዩ ደምሴ ቃለ ጉባኤውን ይይዛሉ፡፡


3፡36 – የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ተወካይ መልካም ምኞታቸውን በንግግራቸው ገልፀዋል፡፡


3፡31 – ” አዲሱን ስራ አስፈፃሚ ለመምረጥ ሃለፊነት እንደተሰጠን ይታወቃል፡፡ እኛም ምርጫው ለማከናውን አጋዥ ናቸው ያላንቸውን ነገሮች አስተካክለን ቀርበናል፡፡ በዚህም መሰረት 4 የፕሬዝደንታዊ እና 22 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተወዳዳሪዎች ተመርጠዋል፡፡ እንደክፍተት ያየነው ማህበራት ተወዳዳሪዎችን ሲያቀርቡ አልተመለከትንም፡፡ ሁሉም በኮታ የሆነ አሰራር አለ፡፡ ይህ በእጅጉ መለወጥ ያለቡት ጉዳይ ነው፡፡ እኛ ተመራጮችን አቅርበናል እናንተ ደግሞ በካርዳችቡ የምትፈልጉትን የመምረጥ መብት አላችሁ፡፡ መልካም ግዜ ተመኘኹ፡፡” አቶ አስጨናቂ


3፡30 – የአስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢው አቶ አስጨናቂ ለማ ንግግር እደረጉ ይገኛሉ፡፡


3፡28 – በአጠቃላይ ከ145 ድምፅ ሰጪዎች መካከል ሁሉም በሰመራ መገኘታቸው ተረጋግጧል፡፡


3፡18 – ምልዐተ ጉባኤው መመሏቱን እየተረጋገጠ ይገኛል፡፡


3:16 – አስመራጭ ጠቅላላ ጉባዔው ተጀምሯል፡፡


3፡16 – የፌደሬሽኑ ዋና ፀሃፊ አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ የመክፈቻ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ሰላም!

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዝዳንታዊ እና ስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ በአፋር ሰመራ እየተካሄደ ይገኛል። ሶከር ኢትዮጵያም ከስፍራው ዋና ዋና ጉዳዮችን በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ ታደርሳለች።