የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምርጫ ከረፋዱ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ እየቀጠለ ይገኛል። አቶ ኢሳይያስ ጂራ ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡበት የዛሬው ምርጫ ረጅም ሰዓት የፈጀው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተከናውኗል።

በምርጫው ከፍተኛ ድምፅ የሚያገኙ እጩዎች በቀጥታ ወደ ኮሚቴው ከመቀላቀል ይልቅ በክልል ውክልና በመሆኑ ቤኒሻንጉል (ሶፊያ አልማሙን) ፣ ደቡብ (ዘሪሁን ቀቀቦ) ፣ አፋር (አሊሚራህ መሐመድ) እና ኢትዮ ሶማሌ (አብዱራዛቅ ሀሰን) በቀጥታ ወደ ኮሚቴው ሲቀላቀሉ ሌሎች አቶ አበበ ገላጋይ (ድሬዳዋ)፣ ኮ/ል አወል አብዱራሂም (ትግራይ) እና ሰውነት ቢሻው (አማራ) ባገኙት ድምፅ መሰረት ተቀላቅለዋል።

ከሀረሪ፣ አአ እና ጋምቤላ የተወከሉ እጩዎች ያገኙት ድምፅ 50+ ባለመሆኑ በድጋሚ ምርጫ የተደረገ ሲሆን አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ የምርጫውን አካሄድ በመቃወም ራሳቸውን ከምርጫው አግልለው ምርጫው ተካሂዷል። በዚህም መሠረት አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ (አአ)፣ አቶ ኢብራሂም መሐመድ (ሀረሪ) እና ቻን ጋትኮት (ጋምቤላ) ኮሚቴውን ተቀላቅለዋል።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት

1 ሶፊያ አልማሙን

2 አበበ ገላጋይ

3 አሊሚራህ መሐመድ

4 ሰውነት ቢሻው

5 ዘሪሁን ቀቀቦ

6 ኮ/ል አወል አብዱራሂም

7 አብዱራዛቅ ሀሰን

8 ዮሴፍ ተስፋዬ

9 ቻን ጋትኮት

10 ኢብራሂም መሐመድ