ሴካፋ የሚያዘጋጀው የክለቦች ውድድር ከዓመታት መቋረጥ በኃላ በሰኔ ወር በታንዛኒያ እንደሚዘጋጅ ታውቋል፡፡ ሆኖም በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን የመወከል እድል ያገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ የመካፈሉ ነገር አጠራጥሯል፡፡
ዛሬ ይፋ በተደረገው የምድብ ድልድል የአምናው የፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ በምድብ 3 ከያንግ አፍሪካ፣ ሲምባ እና ዳካዳህ ጋር ተደልድሏል፡፡ የመጀመሪያውን ጨዋታውንም ሰኔ 22 ያንጋን በመግጠም እንደሚጀምር የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል፡፡
ሆኖም ሊጠናቀቅ የዛሬን ጨምሮ 6 ጨዋታዎች የሚቀሩት ፕሪምየር ሊጉ እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ቀሪ ግጥሚያዎች እያሉ ይህ ውድድር መሰናዳቱን ተከትሎ የፈረሰኞቹ በካጋሜ ዋንጫው ላይ የመሳተፍ ጉዳይ እጅግ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ክለቦች በውድድሩ ታሪክ ዋንጫ አሸንፈው የማያውቁ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁበት ውጤት በትልቅነት ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በተዘጋጀው የሴካፋ ካጋሜ ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያን ወከሎ ለመጨረሻ ግዜ የተሳተፈው አዳማ ከተማ ነበር፡፡
ሙሉ ድልድል
ምድበ 1
አዛም (ታንዛኒያ)
ዩጋንዳ ክለብ
ጄኬዩ (ዛንዚባር)
ካቶር (ደቡብ ሱዳን
ምድብ 2
ራዮን ስፖርት (ሩዋንዳ)
ጎር ማሂያ (ኬንያ)
ሊዲያ ሉዲች (ቡሩንዲ)
ፖርትስ (ጅቡቲ)
ምድብ 3
ያንግ አፍሪካ (ታንዛኒያ)
ሲምባ (ታንዛኒያ)
ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ)
ዳካዳህ (ሶማልያ)
የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታዎች
ሰኔ 22/2010
ያንግ አፍሪካንስ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰኔ 25/2010
ሲምባ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰኔ 28/2010