ሳሙኤል አለባቸው ኮንትራቱን አራዘመ

የዳሽን ቢራው አማካይ ሳሙኤል አለባቸው (ጊቻው) ከዳሽን ቢራ ጋር ለቀጣዮቹ ሁለት የውድድር ዘመናት መፈረሙን በግል የፌስቡክ ገፁ ላይ አስታውቋል፡፡

ተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አጋማሽ የዝውውር መስኮት ከመከላከያ ጋር ያለውን ውል ሰርዞ ለዳሽንቢራ ከፈረመ ወዲህ በጎንደሩ ክለብ የአማካይ ክፍል ድንቅ አገልግሎትን አበርክቷል፡፡

ተጫዋቹ ለዳሽን የፈረመው የ6 ወር ኮንትራት ባለፈው ወር ማለቁን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ ከተለያዩ ክለቦች የዝውውር ጥያቄ ቢቀርብለትም ከዳሽን ጋር ያለውን ኮንትራት አራዝሟል፡፡

የቀድሞው የመብራት ኃይል እና መከላከያ አማካይ ‹‹ ጊቻው › ለኮንራትራት ማራዘምያው የተከፈለው ገንዘብ ይፋ አልሆነም፡፡

ያጋሩ